Theology of the Church, Amharic Student Workbook
1 3 4 /
የ ቤ ተ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሥ ነ - መ ለ ኮ ት
³ የቤተ ክርስቲያን የተሐድሶ ምልክት በመጽሐፍ ቅዱሳዊ ፣ ቤተክርስቲያን ሥርዓት እና በሥርዓተ አምልኮ መመዘኛዎች ላይ ያተኩራል፤ “ቤተ ክርስቲያን የምትኖረው ቃሉ በትክክል የሚሰበክበት፣ የቤተክርስቲያን ሥርዓት በትክክል የሚፈጸምበት፣ እና ተግሣጽ በትክክል በሚታዘዝበት ነው። ³ የቅዱስ ቪንሴንት አገዛዝ (ወይም የቪንሴንቲያን ደንብ) የሚያተኩረው አንዳንድ ሃሳቦች ወይም እውነት በቤተክርስቲያኑ ውስጥ ስልጣን አላቸውብለን የምንፈርጅበትን መመዘኛዎች በማግኘት ላይ ነው። ሲነበብም፤ “በየትኛውም ቦታ፣ ሁልጊዜ፣ እና በሁሉም ዘንድ የታመነው” ይላል። ይህ ደንብ አንዳንድ ትምህርቶች ወይም ልምምድ ከእውነተኛዋ “ታላቅ ባህል” ካላት ክእንዷ የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ትምህርት ጋር መስማማታቸውን ለማወቅ የምንችልበትን አስተማማኝ መንገድ ያቀርባል። ³ በአዲስ ኪዳን የተለያዩ የቤተክርስቲያን ምስሎችን በመረዳት እና በማጥናት ስለ ቤተክርስቲያን ተፈጥሮ እና ተግባር፣ በአለም ላይ ስላላት ተልእኮ እና ስራ ብዙ ማወቅ እንችላለን። ³ የቤተክርስቲያኑ ዋና ስራ በማህበረሰብ ህይወቷ ውስጥ የእግዚአብሔርን ስራ ማስረጃ ማቅረብ ነው፦ የቤተክርስቲያን የመጀመሪያ ስራ በህይወቷ እና በግንኙነቷ ውስጥ የእግዚአብሔርን መልካምነት ማወጅ ነው። ወሳኝ ማንነት የሚገኘው አንድን ነገር በመሆን ነው እንጂ አንድን ነገር በማድረግ ብቻ አይደለም። ቤተክርስቲያን እንደ እግዚአብሔር ሰዎች በመጀመሪያ እሷን የፈጠራት የእርሱን ክብር የሚያንፀባርቅ የህይወት ጥራት ለማሳየት ተጠርታለች። ³ በቤተክርስቲያን ምስል ውስጥ እንደ እግዚአብሔር ቤተሰብ እና ቤት እንዲሁም በአንድነት እንደ ወንድሞችና እና እህቶች በእግዚአብሔር እንደተወደደ ውድ ቤተሰብ መኖር እንዳለብን እናያለን። ³ በአለም ውስጥ ያለ የክርስቶስ አካል እንደመሆኗ ቤተክርስቲያን በአባሎቿ እና በጎረቤቶቿ መካከል ባለን ግንኙነት የኢየሱስን ህይወት ልትለብስ ይገባል። ³ ቤተ ክርስቲያን የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ እንዲሁም የቅድስና እና የመታዘዝን ሥራ ለመከታተል የተጠራው ቅዱስ ሕዝብ እና የእግዚአብሔር ስም የሚታወቅበት እና የሚከብርበት ቅዱስ ስፍራ ናት። ³ እንደ የክርስቶስ አምባሳደሮች፣ ቤተክርስቲያን በአለም ውስጥ የእግዚአብሔርን ስልጣን እና ግዛት እንድትወክል ተጠርታለች በተጨማሪም የመንግስቱን የጽድቅ አገዛዝ በነጻነት፣ በሙሉነት እና በፍትህ ስራዎች እንድታሳይ ተጠርታለች። ³ ቤተክርስቲያን በበጉ ጦርነት የእግዚአብሔር ወታደር ሆና ውግያ ለማድረግ፣ በክርስቶስ የእግዚአብሔርን እውነት በማወጅ፣ የዲያብሎስን ስራ ለማፍረስ ከቃሉ ጋር በመስራት እና ክፉን በመልካም በማሸነፍ ሀላፊነቷን በመውሰድ የእግዚአብሔር ሰራዊት ተብላ ተገልጻለች።
4
Made with FlippingBook - professional solution for displaying marketing and sales documents online