Theology of the Church, Amharic Student Workbook
/ 1 3 5
የ ቤ ተ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሥ ነ - መ ለ ኮ ት
ስለ ቤተክርስቲያን ማንነት እና ስራ ያለዎትን ግንዛቤ በተመለከተ ጥያቄዎችዎን ከተማሪዎችዎ ጋር ለመወያየት ጊዜው አሁን ነው። በቤተክርስቲያን ሚና እና ሃብት ላይ ባላችሁ አመለካከት የራሳችሁ ህይወት እና አገልግሎት በእጅጉ ይነካል። ከቤተክርስቲያን ጋር የተያያዙ የበለጸጉ እውነቶችን ሙሉ በሙሉ ማድነቅዎ በጣም አስፈላጊ ነው። እንደ መሪዎች፣ የእኛ ተግባር በቤተክርስቲያን ውስጥ ያሉ ሌሎች ስጦታቸውን እና በአካሉ ውስጥ ያላቸውን ሚና እንዲያውቁ መርዳት ነው በመሆኑም እያንዳንዱ በተገቢው ቦታ ሲሰራ በክርስቶስ በነገር ሁሉ እንድናድግ ይረዳናል። እርስዎ እራስዎ በአለም ላይ ቤተክርስትያን ስላላት ማንነት እና ተግባር ዝቅተኛ ወይም የተሳሳተ አመለካከት ካልዎት ሌሎች የቤተክርስቲያንን አስፈላጊነት እንዲረዱ ማገዝ አይቻልም። የቤተክርስቲያንን በአለም ላይ ያላትን ሚና የበለፀገ እና የተሟላ ግንዛቤ ላይ ለመድረስ የሚረዱዎትን ልዩ የራስዎን የጥያቄዎች ዝርዝር ያዘጋጁ። አሁን ካጠናኸው ጽሑፍ አንጻር ምን ልዩ ጥያቄዎች አሉህ? ምናልባት ከዚህ በታች ያሉት አንዳንድ ጥያቄዎች የራስዎ የሆኑ ይበልጥ ግልጽ እና ወሳኝ የሆኑ ጥያቄዎችን እንዲፈጥሩ ሊረዱዎት ይችላሉ። * እራሳችንን በእነዚህ “ከመጽሐፍ ቅዱሳዊ ውጪ” በሆኑ መመዘኛዎች ስለቤተክርስቲያኑ (ማለትም፣ የኒቂያ፣ የተሃድሶ እና የቪንሴንቲያን መመዘኛዎች እና ደንቦች) ተግባራዊ ማድረግ እስከ ምን ድረስ ነው አስፈላጊነቱ? እነዚህን መመዘኛዎች መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ቤተክርስቲያን ሚና እና ሥራ በቀጥታ ከሚያስተምረው ጋር ያለውን ግንኙነት እንዴት ልንረዳውና ልናስቀጥለው ይገባናል? * እነዚህን መመዘኛዎች እና ደንቦች እኛ በምናገለግልባቸው ጉባኤዎች ውስጥ ላሉ ሌሎች ሰዎች የምናስተምርበት ከሁሉ የተሻለው መንገድ ምንድን ነው? አባሎቻችንን “በታላቁ ባህል” አስተምህሮ ፤ በትልቁ የክርስቲያን አካል ትምህርቶችና ማስተማር ለእኛ ምን ያህል አስፈላጊ ነው? * አንዳንድ የቤተክርስቲያን መመዘኛዎች እና ምስሎች እንዲሁም ስራዎቿ ከሌሎቹ በበለጠ ከተማን ይመለከታሉ? አብራራ። * እነዚህን መመዘኛዎችና ምስሎች እንኳ በመጠቀም “እውነተኛውን ቤተ ክርስቲያን” ወይም “እውነተኛውን ጉባኤ” መለየት ይቻላልን? ክርስቲያኖችና ጉባኤዎች እግዚአብሔር ለሕይወታቸው ባለው ፈቃድ እንዲያድጉ በመርዳት ረገድ እነዚህን መመዘኛዎች ለመጠቀም ከሁሉ የተሻለው መንገድ ምንድን ነው? * ጌታ በብሉይ ኪዳን እና በአዲስ ኪዳን ብዙ የቤተክርስቲያን ምስሎችን ለእኛ የመስጠቱ ፋይዳው ምንድን ነው? ከብዙ የቤተክርስቲያኗ ሥዕሎች ጋር በተያያዘ ምን ለማድረግ መፈለግ አለብን - እርስ በርሳቸው እንዲዋሃዱ ወይም በራሳቸው እንዲረዱ ወይም ሁለቱንም? * እነዚህን ምስሎች በስብከታችን፣ በትምህርት እና በደቀ መዝሙር ኣድራጊነት ይህም እኛ በምንመራው በተሻለው የቤተክርስትያን ምስል የምንጠቀማቸው እንዴት ነው?
የተማሪው ትግበራ እና አንድምታዎች
4
Made with FlippingBook - professional solution for displaying marketing and sales documents online