Theology of the Church, Amharic Student Workbook
1 3 6 /
የ ቤ ተ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሥ ነ - መ ለ ኮ ት
ጥናቶች
እኛ እና እኛ ብቻ አንድ ማኅበረ ምእመናን በክፉ እና በሚያሳምም የቤተ ክርስቲያን መለያየት ከተቋቋመ በኋላ ከሌሎች አብያተ ክርስቲያናት ጋር ባለው ግንኙነት እየታገለ ነው። አመራሩ ከሌሎች አብያተ ክርስቲያናት ጋር ለኅብረት እና ለአገልግሎት ግንኙነት መፍጠር የሚለውን ሃሳብ ሙሉ በሙሉ ባይተወውም የአዲሱን ጉባኤ አባልነት ማደግ እና ማረጋጋት አስፈላጊነት በእጅጉ ያሳስባቸዋል። መለያየት ከተፈጠረ ከ10 ወራት በላይ አልፏል፤ በዚያን ጊዜ ሁሉ አዲሱ ጉባኤ ከሌሎች ክርስቲያኖች ጋር ለኅብረት እና ለእድገት የሚገናኝበት አንድም ክስተት አልነበረም። አንዳንድ የጉባኤው አባላት ቤተክርስቲያኗን ከሌሎች ጉባኤዎች በማግለል መረጋጋት ማምጣት አስፈላጊ ስለመሆኑ የመሪዎች ውሳኔ ላይ ጥያቄ ማቅረብ ጀምረዋል። በዚህ ሳምንት ትምህርት የተማርናቸው መስፈርቶች እና ምስሎች ይህ ታዳጊ ጉባኤ አሁን ካለው ትግል ጋር እንዴት ይዛመዳሉ? ከመመዘኛዎቹ እና ምስሎች አንጻር ምን ማድረግ አለባቸው? ክርስቲያኖች ጦርነትን አያደርጉም የወጣቶቹ ቡድን መንፈሳዊ ጦርነትን እና የእግዚአብሔር ወታደር መሆናችንን በሚያጎላ ሥርዓተ ትምህርት ውስጥ እያለፈ በመሆኑ አንዳንድ ቤተሰቦች ልጆቹ ስለሚማሩዋቸው ቃላት እና የጦርነት ምስል እንዲሁም በወጣቶች ቡድን ውስጥ ልያደርስ ስለሚችለው ኣሉታዊ ተፅዕኖ መጨነቅ ጀምረዋል። የሽምቅ ውጊያ፣ የቦምብ፣ የሰይፍ፣ የጋሻ፣ የጨለማ ሃይሎች፣ ወዘተ ምስሎች፤ ይህም የወጣቶች ፓስተር ዝም ብሎ ቤተክርስትያን የእግዚአብሔር ሰራዊት እንደሆነች የቤተክርስቲያንን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ምሳሌያዊ አነጋገር አንብቦ ሩቅ እየወሰደ ነው ወይስ አይደለም ብለው በሚያስቡ አንዳንድ ወላጆች ስጋት ሆነዋል ። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያለን ምስል በመጠቀም ትምህርታችንን፣ ማንነታችንን እና በቤተክርስቲያን ውስጥ ያለውን እንቅስቃሴ ለመወሰን በጣም ርቀን ስንሄድ ምን አይነት መመሪያዎችን መጠቀም አለብን? ውስን ይሁኑ። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሥላሴን አላይም በስራ ቦታ ለአንድ የአሃዳዊ ሃይማኖት ተከታይ እምነቱን ሲያካፍል ራልፍ በኢየሱስ ክርስቶስ ያለውን የእግዚአብሔር ፍቅር እየተረከ ነበር በዚያን ጊዜም ሲያካፍልለት የነበረው ሰው በድንገት እንዲህ አለ፡- “በመደበኛው ቤተ ክርስቲያን ያላችሁ ብዙዎቻችሁ ሙሉ በሙሉ ግራ ገብ ቷችኋል”። ስለ እግዚአብሔር፣ ኢየሱስ እና መንፈስ ቅዱስ እንደ ሥላሴ ትናገራላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስን ቢያንስ ስድስት ጊዜ አንብቤአለሁ፤ ስለ ሥላሴ ምንም ዓይነት ትምህርት አጋጥሞኝ አያውቅም። “ሥላሴ” የሚለው ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንኳን አልተጠቀሰም። መጽሐፍ ቅዱስን እንወክላለን ትላላችሁ እኔ ግን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሥላሴን አላየሁም!” ቤተክርስቲያን ስለ ሥላሴ ያላትን አመለካከት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ብቻ ሳይሆን ከቤተክርስቲያንም ትውፊት ጋር ለምን የሚጣጣም እንደሆነ እንዲረዱት የኒቂያን የሃይማኖት መግለጫ፣ የተሃድሶ ምልክቶችን ወይም የቪንሴንቲያን ደንብ መመዘኛዎችን እንዴት መጠቀም ይችላሉ/ትችላላችሁ?
1
2
4
3
Made with FlippingBook - professional solution for displaying marketing and sales documents online