Theology of the Church, Amharic Student Workbook

/ 1 5 3

የ ቤ ተ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሥ ነ - መ ለ ኮ ት

አ ባ ሪ 9 “ወንዝ አለ”

በከተማ ውስጥ የታደሰ እውነተኛ የክርስቲያን ማህበረሰብ ዘርፎችን መለየት ቄስ ዶ/ር ዶን ኤል ዴቪስ • መዝሙር 46.4 (ESV) - “የወንዝ ፈሳሾች የእግዚአብሔርን ከተማ ደስ ያሰኛሉ፤ ልዑል ማደሪያውን ቀደሰ።”

ትክክለኛው ታሪካዊ የመጽሐፍ ቅዱስ እምነት ያላቸው ገባሮች

እንደገና ትኩረት ያገኘ የመንግሥቱ ሥልጣን

የታወቀ የመጽሐፍ ቅዱስ ማንነት የተነቃቃ የከተሞች መንፈሳዊነት

የተረጋገጠ ታሪካዊ ትስስር

ቤተክርስቲያን ካቶሊክ (አለማዓቀፋዊት) ናት

ቤተክርስቲያን አንድ ናት

ቤተክርስቲያን ቅድስት ናት

ቤተክርስቲያን ሐዋርያዊት ናት

ወደ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ታማኝነት የቀረበ ጥሪ ቅዱሳት መጻሕፍትን እንደ ክርስቲያን እምነት እና አሠራር መልህቅ እና መሠረት አድርጎ እውቅና መስጠት

ወደ መንፈስ ቅዱስ ነፃነት ፣ ኃይል እና ሙላት ጥሪ በክርስቶስ አካል ውስጥ በመንፈስ ቅዱስ ቅድስና ፣ ኃይል ፣ ሥጦታ እና ነፃነት መመላለስ

ወደ ታሪካዊ መነሻዎች እና ቀጣይነት ጥሪ እውነተኛውን የክርስትና እምነት የጋራ ታሪካዊ ማንነት እና ቀጣይነት ማወጅ

ወደ ሐዋርያዊ እምነት ጥሪ የሐዋርያዊ ትውፊትን ለክርስቲያናዊ ተስፋ እንደሥልጣን መነሻ ማረጋገጥ

እንደ እግዚአብሔር ህዝብ ፣ እንደ ስደተኞች እና መጻተኞች ለመኖር የቀረበ ጥሪ እውነተኛውን የክርስቲያን ደቀ መዝሙርነት በእግዚአብሔር ሕዝቦች መካከል እንደ ታማኝ አባልነት መተርጎም የቅዳሴ ፣ የቅዱስ ቁርባን እና የሃይማኖታዊ መመሪያዎች አስፈላጊነት ጥሪ በቃሉ ፣ በቅዱስ ቁርባን እና በመመሪያው ዐውድ ውስጥ የእግዚአብሔርን መገኘት መለማመድ

ወደ መሲሐዊው መንግሥት ማንነት ጥሪ በናዝሬቱ ኢየሱስ ውስጥ የተስፋውን መሲሕ እና የመንግሥቱን ታሪክ እንደገና ማግኘት

የቅዱሳንን ዓለም አቀፍ ኅብረት ለማረጋገጥ እና ለመግለጽ የቀረበ ጥሪ በአካባቢያዊም ሆነ በዓለም ዙሪያ ካሉ ሌሎች አማኞች ሁሉ ጋር ትብብር እና ትብብርን መግለጽ

ለተወካይ ባለስልጣን የቀረበ ጥሪ እንደ እውነተኛ የእምነት እረኞች በቤተክርስቲያን ውስጥ የእግዚአብሔር ስጦታ ላላቸው አገልጋዮች በደስታ መገዛት

ለመልካም መስተንግዶ እና ለመልካም ስራዎች የቀረበ ጥሪ የመንግሥቱን ፍቅር ለሁሉም ፣ በተለይም ለእምነት ቤተ ሰዎች መግለፅ

የትንቢታዊ እና ሁለንተናዊ ምስክርነት ጥሪ ለጎረቤቶቻችን እና ለሁሉም ህዝቦች ክርስቶስን እና መንግስቱን በቃል እና በተግባር ማወጅ

የሃይማኖታዊ ዝምድና ጥሪ የቂያ የሃይማኖት መግለጫን እንደ ታሪካዊ ቀጥተኛ የጋራ የእምነት ሕግ አድርጎ መቀበል

ይህ ንድፍ በግንቦት 1977 "ዘቺካጎ ኮል" በተሰኘ መግለጫ ግንዛቤ ላይ የተመሠረተ ሲሆን የተለያዩ ታዋቂ የወንጌላውያን ምሁራንና ባለሙያዎችም የተገናኙበትና ዘመናዊው የወንጌል ስርጭት አገልግሎት ከታሪካዊው የክርስትና እምነት ጋር ስላለው ዝምድና የተወያዩበት ነው ፡፡

Made with FlippingBook - professional solution for displaying marketing and sales documents online