Theology of the Church, Amharic Student Workbook

2 2 /

የ ቤ ተ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሥ ነ - መ ለ ኮ ት

እነዚህን እና ሌሎች ቪዲዮው ያነሳቸውን ጥያቄዎች ለመመለስ አስፈላጊውን ያህል ጊዜ ውሰድ። ለመጀመር ያህል እግዚአብሔር ለራሱ ክብርና ሞገስ ለማምጣት ስላለው ዓላማ፣ እና ይህም ሰዎችን ከምድር ለራሱ ለመቤዠት ካለው ከፍተኛ ዓላማ ጋር እንዴት እንደሚዛመድ ግልጽ መሆን አለብን። እግዚአብሔር ከአብርሃም ጋር በገባው ቃል ኪዳን፣ የአህዛብ የወንጌል ተሳትፎን በሚመለከት ምስጢሩ መገለጥ እና የራሱን ሰዎች መፈጠር፣ ስለሚመጣው አዲሱ የሰው ልጅ ምስል፣ ስለ ዘላለማዊ አላማው ግልፅ ፍንጭ ይሰጣል። መልሶችህ ግልጽ እና አጭር ይሁኑ፣ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ደግሞ በቅዱሳት መጻሕፍት አስደግፍ! 1. በእርሱ በኩል የምድር ነገዶች ሁሉ እንዲባረኩ እግዚአብሔር ከአብርሃም ጋር ቃል ኪዳን የገባው በምን መንገድ ነው? 2. እግዚአብሔር ስለ ፍጥረታቱ፣ ራሱን ስለመግለጡ እና ሌሎችን ለእርሱ ቤዛ አድርጎ ስለመውሰዱ የቅዱሳት መጻሕፍት ምስክርነት ምንድ ነው? እግዚአብሔር አጽናፈ ሰማይን ለምን ፈጠረው? 3. በሮሜ 16፣ ኤፌሶን 3 እና ቆላስይስ 1 ላይ የእግዚአብሔርን የመቤዠት አላማ በተመለከተ የተነገረው ምስጢር ምን አይነት ነው? 4. እግዚአብሔር ሰዎችን ከምድር ለራሱ ለማውጣት ካለው ዓላማ ጋር በተያያዘ ከአህዛብ ጋር ስላለው ዓላማ ምን ገልጿል? ይህ ዓላማ እግዚአብሔር ከአብርሃም ጋር በገባው ቃል ኪዳን ውስጥ የሚታየው እንዴት ነው? 5. እስራኤል መሲሑ ወደ ዓለም እንዲመጣ የእግዚአብሔር መሣሪያ የሆነችው በምን መንገድ ነው? እስራኤል ከእግዚአብሔር ጋር ባላት ግንኙነት የእግዚአብሔርን ሕዝብ፣ የቤተክርስቲያንን ግልጽ ገጽታ እንዴት ትገልጣለች? 6. ሐዋርያት የእስራኤልን ተስፋ በኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ቤተክርስቲያን ላይ እንዴት ይተገብራሉ? ምሳሌዎችን ስጥ። 7. በክርስቶስ በኩል ያለችው ቤተክርስቲያን በእግዚአብሔር የማዳን እቅድ ውስጥ ልዩ ቦታ ተሰጥቷታል። እንግዲህ የእስራኤል ቦታ እንደ እግዚአብሔር ሕዝብ ምንድር ነው? እግዚአብሔር እስራኤልን ትቷታልን ወይስ መመረጧን ሰርዟል? አብራራ።

መሸጋገሪያ 1

የተማሪው ጥያቄዎች እና ምላሾች

1

Made with FlippingBook - professional solution for displaying marketing and sales documents online