Theology of the Church, Amharic Student Workbook
/ 2 3
የ ቤ ተ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሥ ነ - መ ለ ኮ ት
በእግዚአብሔር እቅድ ጥላ ውስጥ ያለች ቤተክርስቲያን ሴግመንት 2፡ መዳን፡ የእግዚአብሔርን ሕዝብ መቀላቀል
ቄስ ቴሪ ኮርኔት
ሴግመንት 2 ማጠቃለያ
በኃጢአት ምክንያት፣ እያንዳንዱ ሰው ተስፋ ቢስ በሚመስል ሁኔታ ላይ ነው። ከኃጢአትና ከሚያስከትላቸው ውጤቶች መዳን በጣም ያስፈልገናል፣ ነገር ግን ኃጢአተኛ ተፈጥሮአችን የእግዚአብሔርን ማዳን እንዳንፈልግ ወይም ከእርሱ ጋር የምንገናኝበት ምንም ዓይነት መንገድ እንዳንይዝ ያደርገናል። በሚያስደንቅ ሁኔታ እግዚአብሔር እኛን እንደ ጠላቶቹ ሊተወን አልመረጠም። ሐዋርያው ጳውሎስ ገና በኃጢአት ቀንበር ስር ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቶአል ሲል ያስተምራል። ወንጌል ለራሳችን ማድረግ ለማንችለው ነገር እግዚአብሔር የሚያድነን ጸጋን እንደሚሰጠን የሚናገር የምሥራች ነው። ይህንን ጸጋ መረዳቱ የቤተክርስቲያን የአምልኮ ማህበረሰብ የመሆንን ሃላፊነት ለመገንዘብ መሰረት ነው። ድነት፡ የእግዚአብሔርን ህዝብ መቀላቀል የተሰኘው የዚህ ሴግመንት አላማችን የሚከተሉትን ማስቻል ነው፡- • ስለ ድነት ሥነ-መለኮታዊ ፍቺ ትሰጥ ዘንድ • ከእግዚአብሔር መለየት የሚያስከትለውን መዘዝ መግለጽ ትችል ዘንድ • ከክርስቶስ ጋር ባለን አንድነት የምናገኛቸውን ጥቅሞች መግለጽ ትችል ዘንድ • ዘፀአት ለክርስቲያን ድነት እንደ ምሳሌ (ዓብነት) እንዴት እንደሚያገለግል ትረዳ ዘንድ • ወደ ቤተክርስቲያን (የእግዚአብሔር ሰዎች) መቀላቀል ድነትን ተከትሎ የሚጨመር ነገር ሳይሆን የመዳን ትርጉም ማዕከል እንደሆነ ማስረዳት ትችል ዘንድ ነው።
1
Made with FlippingBook - professional solution for displaying marketing and sales documents online