Theology of the Church, Amharic Student Workbook
4 4 /
የ ቤ ተ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሥ ነ - መ ለ ኮ ት
ነገር ሳያቀርብ ወደ እግዚአብሔር ፊት መምጣት አለመቻሉ ነው። እግዚአብሔር የእኛን ምርጡን፣ የላቀውንና በጣም ውዱ መስዋዕታችን ይገባዋል፣ ይልቁንም ከስጦታዎቻችንና ከነገሮቻችን በላይ እኛ ራሳችን ሁለንተናችን ይገባዋል። እጅግ ደስ በሚያሰኙና ነገሮች መልካም በሚሆኑባቸው በእነዚያ ጊዜያት ብቻ ሳይሆን ከባድ መከራና ፈተና በሚደርስብንም ጊዜ እንኳ ለእርሱ የላቀ ምስጋናችንን ልናቀርብለት ይገባል። አምላካችን የማይለወጥ አምላክ ነው፣ በሕይወታችንና በአገልግሎታችን ውስጥ ደስ የማያሰኙ ነገሮች እየተከናወኑ ቢሆንም እንኳ እርሱ ሊመለክ ይገባዋል። ከፍጡራን ሁሉ በላይ ከፍ ከፍ ያለው እርሱ ጌታ እግዚአብሔር ነው፣ በላቀ ትኩረትና ኃይላችን፣ በምርጥ መዝሙሮቻችን፣ በሕያው ሽብሸባችን፣ በታላቁ አገልግሎታችንና በሁለንተናዊ ምላሻን አምልኳችን ይገባዋል። በአምልኮ ላይ ያለች ቤተክርስቲያን ደግሞ ዘወትር ለእርሱ ለቅድስናው የሚስማማና ለክብሩ የሚመጥንን መስዋዕት ታቀርባለች። በእርግጥ እርሱ በእውነት ሊመለክና ምስጋናችንን ሊቀበል ይገባዋል። ዕንባ. 3፡17-19 ምንም እንኳ በለስም ባታፈራ፥ በወይንም ሐረግ ፍሬ ባይገኝ፥ የወይራ ሥራ ቢጐድል፥ እርሾችም መብልን ባይሰጡ፥ በጎች ከበረቱ ቢጠፉ፥ ላሞችም በጋጡ ውስጥ ባይገኙ፥ [18] እኔ ግን በእግዚአብሔር ደስ ይለኛል፤ በመድኃኒቴ አምላክ ሐሤት አደርጋለሁ። [19] ጌታ እግዚአብሔር ኃይሌ ነው፤ እግሮቼን እንደ ዋላ እግሮች ያደርጋል፤ በከፍታዎችም ላይ ያስሄደኛል። ነቢዩ ዕንባቆም ለእግዚአብሔር የምስጋናን መስዋዕት ከማቅረብ አንጻር መንገዱን ያሳየናል፡-
2
ስለዚህ የዕብራውያን ጸሐፊ የተናገረውን ቃል እንከተል፡-
ዕብ. 13፡15፡ 15 እንግዲህ ዘወትር ለእግዚአብሔር የምስጋናን መሥዋዕት፥ ማለት ለስሙ የሚመሰክሩ የከንፈሮችን ፍሬ፥ በእርሱ እናቅርብለት።
የኒቂያን የእምነት መግለጫ (በአባሪው ውስጥ ይገኛል) ካነበብክ እና/ወይም ከዘመርክ በኋላ የሚከተለውን ጸሎት ጸልይ፥ የዘላለም አምላክ አባታችን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ሆይ፡ አንተ ብቻ ምስጋና ይገባሃል ስለዚህ ክብርና ውዳሴ፣ ምስጋናም እንድናቀርብልህ ትጠብቅብናለህ። በፍጹም ልባችን በደስታ የሆነን አምልኮ በሁሉም ስብሰባዎቻችን፣ በሁሉም ግንኙነቶቻችን እናቀርብልህ ዘንድ የመንፈስን ኃይል እንድትሰጠን በተወደደ ልጅህ በአዳኛችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እንጠይቃለን። በሁሉም ተግባሮቻችን እና በሁሉም አገልግሎቶቻችን ውስጥ የምንናገረውንና የምናደርገው ሁሉ እንደ ጌታ አምላካችን ለምስጋናና ለክብር የተሠዋ መስዋዕት አድርገህ ትቀበለው ዘንድ በኢየሱስ ስም እንጸልያለን አሜን።
የኒቅያ የእምነት መግለጫ እና ጸሎት
Made with FlippingBook - professional solution for displaying marketing and sales documents online