Theology of the Church, Amharic Student Workbook

/ 4 5

የ ቤ ተ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሥ ነ - መ ለ ኮ ት

ማስታወሻዎችህን አስቀምጥ ፣ ሀሳብህን ሰብስበህ በእግዚአብሔር እቅድ ውስጥ ያለች ቤተክርስትያን የተሰኘውን የትምህርት 1ን ፈተና ውሰድ።

ፈተና

የቃል ጥናት ክፍል ቅኝት

ከሌላ ሰው ጋር በመሆን ላለፈው ክፍለ ጊዜ የተመደበውን የቃል ጥናት ክፍል ፃፍ ወይም በቃልህ አንብብ: 1 ጴጥ 2.9-10

ባለፈው ሳምንት ለተሰጠው የንባብ የቤት ስራ መምህርህ የሚጠብቅብህን ዋና ዋና ነጥቦችና ማጠቃለያ አቅርብ (ንባብ ማጠናቀቂያ ገጽ)።

የቤት ስራ ማስረከቢያ

እውቂያ

ጸጋ በሰው ባህሪ ላይ ጥናት ሲያደርግ ስለነበረ ሰው ታሪክ ሰማሁ። ይህ ሰው በአንድ ትልቅ ከተማ ውስጥ በሚገኝ ነዳጅ ማደያ ውስጥ ከፓምፖች አጠገብ ቆሞ ወደ ማደያው ለሚመጡ ሰዎች የሃያ ዶላር ደረሰኞች ይሰጥ ነበረ። የሚገርመው ማንም ገንዘቡን አይወስድም ነበር። በከተሞች ውስጥ የምንኖር ሰዎች በዚህ ምላሽ ብዙም ላንደነቅ እንችል ይሆናል። በትልልቅ ከተሞች ውስጥ ያሉ አብዛኞቹ ሰዎች “ምንም ነገር እንዲሁ በነጻ አታገኙም” የሚለውን እና አንድ ሰው የሆነ ዋጋ ያለው ነገር በነጻ የሚሰጥ ቢሆን እውነት ሊሆን አይችልም የሚለውን አመለካከት በአንድም ይሁን በሌላ ተምረዋል። እኛ የከተማ ነዋሪዎች አንድ ነገር በጣም እውነት መስሎ ከታየን ሁልጊዜም ጥሩ ነው ማለት ነው ብለን እንወስደዋለን። በነፃ ስለምናገኛቸው ነገሮች ጠርጣራ መሆን ለኛ ተፈጥሯዊ ነው። የዛሬው ትምህርት አምልኮ ለእግዚአብሔር ፀጋ ምላሽ ስለመሆኑ ነው። ወንጌል የሚያስፈልገንና ሊኖረን የማይችለው ነገር ሁሉ ከእግዚአብሔር የተሰጠን የጸጋ ነጻ ስጦታ ስለመሆኑ የምስራች ነው። በነዳጅ ፓምፖች ውስጥ እንደነበሩት ሰዎች የእግዚአብሔር ጸጋ ፍፁም ነፃ ስጦታ መሆኑን መጀመሪያ ላይ አንገነዘብም። የመዳን ስጦታ በስራ ፈጽሞ ሊገኝ እንደማይችል እና እንደ ስጦታ ብቻ የምንቀበለው ስጦታ እንደሆነ ለመጀመሪያ ጊዜ የተገነዘብከው መቼ ነው? ትንሽ ርቆ መሄድ ቤተ ክርስቲያንህ ይህንን ጥያቄ መመለስ ካለባት እንዴት ትመልሰዋለች፡- “ሁሉም የአምልኮና የውዳሴ አይነቶች ለእግዚአብሔር እንዲቀርቡ ታዝዘዋል፣ እኛ ግን ሌሎችን (X) ለማሳተፍ አምልኮንን ትንሽ ራቅ አድርገን ወስደነዋል።” በአንዳንድ የቤተክርስቲያናችን አውድ ውስጥ ተቀባይነት ካለው የአምልኮ ወሰን በላይ መሄድ በእናንተ ጉባኤ ውስጥ ምን ማለት ነው? በአምልኳችን ላይ ገደቦች ሊኖሩን ይገባል፣ እናም ከሆነስ በክርስቶስ ካለን ነፃነታችንና ለእግዚአብሔር ያለንን ፍቅራችንን አዲስና ልዩ በሆነ መንገድ ለመግለጥ ካለን ፍላጎት ጋር በተያያዘ አንዳንድ ገደቦችን ለማስቀመጥ ቢያስፈልግ መመዘኛዎቹ ምን መሆን አለባቸው?

1

2

2

Made with FlippingBook - professional solution for displaying marketing and sales documents online