Theology of the Church, Amharic Student Workbook
/ 4 9
የ ቤ ተ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሥ ነ - መ ለ ኮ ት
ሐ. ገላ. 2.21
መ. እኛ የምናደርገው ማንኛውም መልካም ስራ ወይም የጽድቅ ስራ በእኛ ውስጥ የሚሰራው የእግዚአብሔር ጸጋ ውጤት ነው። መልካም ሥራ የመዳን ምክንያት ሳይሆን የመዳን ውጤት ነው። የትኛውም መልካም ሥራችን በእግዚአብሔር ፊት ምንም አይነት ተጨማሪ ሞገስ አያገኝልንም። ማንም ሰው ከእግዚአብሔር ጋር ህብረት ወይም ከእርሱ ጋር በመንግሥቱ ውስጥ የዘላለም ሕይወት ለማግኘት ብቁ ሊሆን አይችልም። በክርስቶስና እርሱ በሰራው ሥራ አማካኝነት የእርሱ ጸጋ በእኛ ላይ ፈስሷል። መልካም ስራችን እግዚአብሔር ለእኛ ስለሰጠው ፀጋ ምላሽ ነው። በድጋሚ ሐዋርያው ዮሐንስ እንዳለው “እርሱ አስቀድሞ ወዶናልና እኛ ደግሞ እንወደዋለን” 1ኛ ዮሐንስ 4፡19
2
II. አምልኮ ለእግዚአብሔር ፀጋ የቤተክርስቲያን ምላሽ ነው። አምልኮ ምንጊዜም የቤተክርስቲያን ዋነኛና አስፈላጊ ኃላፊነት ነው ምክንያቱም በጸጋ ለመኖር መነሻ ነው። በአምልኮ ውስጥ ያዕቆብ በመልእክቱ እንደጻፈው፣ “በጎ ስጦታ ሁሉ ፍጹምም በረከት ሁሉ ከላይ ናቸው፣ ከብርሃናት አባት ይወርዳሉ” ያዕ 1፡17።
ሀ. በክርስቲያናዊ አምልኮ ውስጥ ሁለት ወሳኝ ክንውኖች (ምግቡ እና መታጠቢያው)
በእያንዳንዱ የክርስትና ባህል ውስጥ የጌታ እራት እና ጥምቀት በመካከላችን የሚሰራውን የእግዚአብሔርን ጸጋ የምንለማመድበት አስፈላጊ ክፍሎች ናቸው። ክርስቲያኖች ግን እነዚህ የአምልኮ ተግባራት በቤተክርስቲያን ውስጥ የእግዚአብሔርን ጸጋ በሚያሳዩበት መንገድ ይለያያሉ። አንዳንድ አብያተ ክርስቲያናት የጌታን እራት እና ጥምቀትን “ምስጢረ ቁርባን” ብለው ይጠሩታል እና እንደ “ጸጋ መንገድ” ይወስዱታል፤ ሌሎች ደግሞ እንደ “ሥርዓት” ይወስዷቸዋል የሚገነዘቡትም እንደ የእግዚአብሔር ጸጋ ምስክርነት ነው። ልዩነቱን ላብራራ፡
ለ. የ“ቅዱስ ቁርባን” ትርጉም
1. ቅዱስ ቁርባን በተለምዶ “የውስጣዊ እና የመንፈሳዊ ጸጋ ውጫዊ እና የሚታይ ምልክት” ተብሎ ይገለጻል። ቅዱስ ቁርባን የሚለውን ቃል የሚጠቀሙ ሰዎች ጥምቀት እና የጌታ እራት የእግዚአብሔር ጸጋ ወደ እኛ የሚመጣበት መንገድ እንደሆነ አድርገው ይመለከቱታል።
Made with FlippingBook - professional solution for displaying marketing and sales documents online