Theology of the Church, Amharic Student Workbook

5 0 /

የ ቤ ተ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሥ ነ - መ ለ ኮ ት

2. ምንም እንኳን ካቶሊኮች እና የምስራቅ ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች ብዙ ቁርባናት ቢኖሯቸውም ፕሮቴስታንቶች ግን አብዛኛውን ጊዜ ቅዱስ ቁርባን የሚለውን ቃል ለጥምቀት እና ለጌታ እራት ብቻ ይጠቀማሉ። እነዚህ ሁለቱ ቁርባናት በቤተክርስቲያን ታሪክ ውስጥ እንደ “የጸጋ መንገድ” ልዩ ቦታ አላቸው ምክንያቱም እነዚህ በቀጥታ የተመሰረቱት በኢየሱስ ትእዛዝ ነው። የጌታን እራት እና ጥምቀትን እንደ ቅዱስ ቁርባን የሚገልጹ ሰዎች እነዚህን በእምነት በሚወስዱበት ወቅት እግዚአብሔር የገባውን ቃል ለመፈጸም በጸጋው በእኛ ውስጥ እየሰራ ነው ብለው ይከራከራሉ።

ሐ. የ“ሥርዓተ አምልኮ” ትርጉም

1. የጌታን እራት እና ጥምቀትን ከቅዱስ ቁርባንነት ይልቅ እንደ ስርአተ አምልኮ የሚረዱ ብዙ የቤተክርስቲያን ባህሎች አሉ። “ሥርዓት” የሚለውቃል “አስገዳጅ ትእዛዝ” ማለት ሲሆን ስለዚህ የጌታእራት እና ጥምቀት የሚከናወኑት የክርስቶስን ትእዛዝ በመታዘዝ ነው። እነዚህ አብያተ ክርስቲያናት ጥምቀት እና የጌታ ራት የእግዚአብሔር ጸጋ ወደ እኛ የሚመጣበት መንገድ ከመሆን ይልቅ እኛ የተቀበልነውን የእግዚአብሔርን ጸጋ የምናስብበት የምንመሰክርበት ነው ብለው ይሞግታሉ።

2

2. ዘጸ. 12.14 - ይህም ቀን መታሰቢያ ይሁናችሁ፥ ለእግዚአብሔርም በዓል ታደርጉታላችሁ፤ ለልጅ ልጃችሁ ሥርዓት ሆኖ ለዘላለም ታደርጉታላችሁ።

3. የአብዛኞቹ የብሉይ ኪዳን አምልኳዊ ስነስርዓቶች ትኩረት ሰዎች በትዕዛዝ ወይም በሃይማኖታዊ ሥነ ሥርዓት መታዘዝን እንዲያስታውሱ መርዳት ነበር። በአዲስ ኪዳን ውስጥ፣ ጥምቀት እና የጌታ እራት እግዚአብሔር በኢየሱስ ሕይወት፣ ሞት እና ትንሳኤ በኩል ለሰጠን ጸጋ የአደባባይ ምስክር ሆነው ያገለግላሉ፤ ቤተክርስቲያንም በዚህ ጸጋ ውስጥ እንዳለችና እንደምትኖር ያስታውሰናል።

Made with FlippingBook - professional solution for displaying marketing and sales documents online