Theology of the Church, Amharic Student Workbook
/ 5
የ ቤ ተ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሥ ነ - መ ለ ኮ ት
የሞጁሉ (የትምህርቱ) መግቢያ
ኃያል በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ሰላም ለአንተ ይሁን፥
በኢየሱስ ክርስቶስ ያለችው የእግዚአብሔር ቤተክርስቲያን ከቅዱሳት መጻህፍት በጣም አስፈላጊ መሪ ሃሳቦች አንዷ ነች። የናዝሬቱ ኢየሱስ በሞቱ፣ በመቀበሩ እና በትንሳኤው በምድር ላይ እሱን እንዲወክሉ እና የመጣውን/ደግሞም የሚመጣውን መንግስቱን እንዲመሰክሩ በተጠሩት በአዲሶቹ ህዝቡ ላይ ራስ ሆኖ ከፍ ከፍ ብሏል። ቤተክርስቲያኑ በእግዚአብሔር መንግሥት ፕሮግራም ውስጥ ያላትን ሚና ለመረዳት ለእያንዳንዱ የግል እና የጋራ ደቀመዝሙርነት ገጽታ ወሳኝ ነው። በቤተክርስቲያን ውስጥ ከእግዚአብሔር የማዳን ተግባር ውጭ ደቀመዝሙርነት ወይም ድነት የለም። እግዚአብሔር በህዝቡ አማካኝነት እና በህዝቡ በኩል የሚያደርገውን መረዳቱ አንድን መሪ እግዚአብሔርን በጥበብ እና በክብር እንዲወክል ኃይል ይሰጠዋል። ዛሬ በአለም ያለውን የአገልግሎት ባህሪ ሙሉ በሙሉ እንድታደንቁ ቤተክርስቲያንን በሚገባ እንድታጠኑ እንጋብዛችኋለን። በእግዚአብሔር እቅድ ጥላ ውስጥ ያለች ቤተክርስቲያን የተሰኘው የመጀመሪያው ትምህርት ቤተክርስቲያን ከአብርሃም ጋር በገባው ቃል ኪዳን አዲስ ሰውን በማዳን ለራሱ ክብርን ለማምጣት በእግዚአብሔር የላቀ አላማ እንዴት እንደምትገለፅ ላይ ያተኩራል። አህዛብን በክርስቶስ ኢየሱስ ባለው ስራው ውስጥ ለማካተት እና የእግዚአብሔርን ላኦስ ለራሱ ልዩ የሆነን ህዝብ ለመፍጠር ባለው ሀሳብ ቤተክርስቲያን ለጸጋው የድነት እቅዱ መገለጥ እንዴት ጥላ እንደምትሆን ትመለከታለህ። በተጨማሪም የድነትን ብልጽግና እና ትርጉም፣ በኃጢአት ምክንያት ከእግዚአብሔር ከመለየትና መጥፋት ያለ መታደግ ምን ማለት እንደሆነ ትገነዘባለህ። ከክርስቶስ ጋር ባለን አንድነት ተስፋ የገባልንን መንግሥት ከሚወርሱት “የእግዚአብሔር ሕዝቦች” ጋር እንተባበራለን። ከክርስቶስ ጋር መተባበር በእግዚአብሔር ላይ ተስፋ ካላቸው ሰዎች ጋር አንድ መሆን ሲሆን ይህም በእግዚአብሔር አገዛዝ ሥር አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር በመፍጠር ኃጢአትና ሞት በዓለም ላይ ያስከተሉትን ውጤት ሙሉ በሙሉ የሚሽር ይሆናል። በአምልኮ ላይ ያለች ቤተክርስቲያን በተሰኘው በሁለተኛው ትምህርታችን ድነትን እንደ ቤተክርስትያን የአምልኮ መሰረት እንቆጥረዋለን። መዳን በእግዚአብሔር ጸጋ ብቻ እንደሚመጣ እና የሰው ልጅ በምንም መንገድ ሊያገኘው ወይም ሊገባው እንደማይችል እናያለን። ስለዚህ አምልኮ ለእግዚአብሔር ጸጋ ትክክለኛ ምላሽ ነው። እንዲሁም ስለ ቤተክርስትያን አምልኮ ከክርስቲያናዊ ነጸብራቅ የተገኙትን አንዳንድ ግንዛቤዎችን እንመረምራለን፣ ይህም “ምስጢረ ቁርባን” እና “ሥርዓት” የሚሉትን ቃላት አጭር ጥናት እንዲሁም ስለ ጥምቀት እና የጌታ ራት በቤተክርስቲያን አምልኮ ላይ ስለሚተገበሩ የተለያዩ አመለካከቶች ጭምር እንመለከታለን። በተጨማሪም የቤተክርስቲያንን አምልኮ ሥነ-መለኮታዊ ዓላማ እናገኘዋለን፣ እርሱም በብቸኝነት ቅድስናው፣ ወሰን በሌለው ውበቱ፣ ተወዳዳሪ በሌለው ክብሩ እና አቻ በሌለው ስራዎቹ የተነሳ እግዚአብሔርን ማክበር ነው። በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ወደ አምላከ ስላሴ በመቅረብ፣ ቤተክርስቲያን በምስጋና እና በውዳሴ፣ እና በሥርዓተ ቅዳሴ ለቃሉና ለምስጢራት አጽንዖት ይሰጣል። ቤተክርስቲያንም እንደ ቃል ኪዳን ማህበረሰብ እግዚአብሔርን በመታዘዟ እና በአኗኗሯ ታመልካለች።
Made with FlippingBook - professional solution for displaying marketing and sales documents online