Theology of the Church, Amharic Student Workbook

6 /

የ ቤ ተ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሥ ነ - መ ለ ኮ ት

ቤተክርስቲያን እንደ ምስክር የተሰኘው ሶስተኛው ትምህርት ደግሞ በቤተክርስቲያን ተልዕኮ ላይ ያተኩራል። በዚህ ትምህርት ውስጥ ለኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ምርጦች የሚለውን ሃሳብ ለተመረጠው ሕዝብ ለእስራኤል እና ለቤተክርስቲያን፣ እንዲሁም ለግለሰብ አማኞች የሚሠራበትን የመመረጥ ትምህርት በጣም አስፈላጊ የሆኑትን ገጽታዎችን እንሸፍናለን። ኢየሱስ ክርስቶስን እግዚአብሔር ከዓለም ሕዝብን ለራሱ እንዳዳነበት እንደ እግዚአብሔር ምርጥ እናገኘዋለን። በተጨማሪም በእግዚአብሔር አስቀድሞ ስለመመረጥ ጽንሰ ሐሳብ ከእስራኤል እንደ እግዚአብሔር ህዝብ እና እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን መሰየም አንጻር የጽንሰ ሃሳቡን ስፋትና ፍቺ በአጭሩ እንቃኛለን። እንደ እግዚአብሔር የታላቁ ተልእኮ መሣሪያ በውስጡ ያሉትን ሦስት ወሳኝ ነገሮች እንመረምራለን፡ እነዚህም ቤተክርስቲያን ለጠፉት ወንጌልን ስትሰብክ፣ አዳዲስ አማኞችን በክርስቶስ ስታጠምቅ፣ ማለትም እነርሱን ወደ ቤተክርስቲያን አባልነት ስታካትት፣ እና ብልቶቿ ክርስቶስ ያዘዘውን ሁሉ እንዲጠብቁ ስታስተምር ናቸው። በመጨረሻም በሥራ ላይ ያለች ቤተክርስቲያን በተሰኘው በትምህርት አራት የቤተክርስቲያንን የተለያዩ ገጽታዎች እና አካላትን እንመለከታለን። የቤተክርስቲያን ድርጊቶች እና የአኗኗር ዘይቤዎች እውነተኛ ምልክቶች በሆኑት የተወሰኑ ምልክቶች ላይ በማተኮር እውነተኛውን የክርስቲያን ማህበረሰብ እንዴት ልንለይ እንደምንችል ልዩ ትኩረት ይሰጣል። የቤተክርስቲያን ምልክቶችን ከኒቂያው የእምነት መግለጫ እና እንዲሁም ከተሐድሶ ትምህርት አንጻር እንቃኛለን። እንዲሁም በክርስቲያኖች ላይ አስገዳጅ ናቸው የሚባሉ ወጎችን እና ትምህርቶችን ለመረዳት እና ለመገምገም አጋዥ መመሪያ በሆነው በቪንሴንሺያን ደንብ መነፅር ቤተክርስቲያንን እንመለከታለን። ይህን ጥናት በአዲስ ኪዳን በተጠቀሱት የእግዚአብሔር ቤተ ክርስትያን ምስሎች (የእግዚአብሔር ቤተሰብ)፣ በክርስቶስ አካል እና በመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ (የእግዚአብሔር መንግሥት ወኪል) ምስሎች ውስጥ በሚኖረው የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ላይ በማተኮር ጥናታችንን እንቋጫለን። ቤተክርስቲያንን በበጉ ጦርነት ውስጥ እንደምትዋጋ የእግዚአብሔርን ሰራዊት እንመለከታለን። እነዚህ ምስሎች ዛሬ በአለም ላይ የቤተክርስቲያንን ማንነት እና ስራ እንዴት ልንረዳ እንደሚገባን ትልቅ ግንዛቤን ይሰጣሉ። ያለ ጥርጥር፣ የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን የእግዚአብሔር የመንግሥቱ እና የመገኘቱ ሰዎች ወኪል ናት። የዚህን ትምህርት እና የእግዚአብሔር ቃል ጥናት በውስጥህ የእግዚአብሔር ህዝብ ለሆኑት ለቅዱሳን ጥቅም ለመኖር እና ለማነጽ ጥልቅ ፍቅርን ይጨምርልህ!

እግዚአብሔር ቅዱስ ቃሉን በትጋት ስለምታጠና አብዝቶ ይባርክህ።

- ቄስ ዶክተር ዶን ኤል ዴቪስ

Made with FlippingBook - professional solution for displaying marketing and sales documents online