Theology of the Church, Amharic Student Workbook

/ 5 3

የ ቤ ተ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሥ ነ - መ ለ ኮ ት

ሐ. ጥምቀት በሁለቱም በቅዱስ ቁርባን እና በሥርዓት ወጎች ውስጥ እኩል አስፈላጊ ነው።

ጥምቀት የተሰጠው እና የታዘዘው በራሱ በክርስቶስ ነው። በፍፁም አማራጭ ወይም የሚተው አይደለም። ስለዚህ እንደ ቅዱስ ቁርባን ለሚመለከቱትም ሆነ እንደ ሥርዓት ለሚመለከቱት፣ ጥምቀት አንድ ሰው ለኢየሱስ ክርስቶስ ጌትነት ራሱን የሰጠበት መለያ ምልክት ነው።

IV. የጌታ እራት

ሀ. የተለመዱ ቃላት፡-

በጌታ እራት ውስጥ በእግዚአብሔር እና በቤተክርስቲያን መካከል ያለውን ቃል ኪዳን ሳያቋርጥ ይታደሳል። ‘ትውስታ’ (አናምኔሲስ) የሚለው ቃል የሚያመለክተው የሰው ልጅ ጌታን ማስታወስ ብቻ ሳይሆን እግዚአብሔር መሲሑንና ቃል ኪዳኑን እንዲሁም መንግሥቱን ለመመለስ የገባውን ቃል ኪዳን ጭምር ማስታወስ ነው። በጌታ እራት ወቅት ይህ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት ከእውነተኛ የምልጃ ጸሎት ጋር ይቀርባል። ~ R. S. Wallace. “Lord’s Supper.” Evangelical Dictionary of Theology. Walter A. Elwell, ed. Grand Rapids: Baker, 1984. p. 653.

1. የጌታ እራት ለዚህ የአምልኮ ተግባር የተለመደ ስም ነው።

2

2. ቅዱስ ቁርባን (ትርጉሙም “የምስጋና ምግብ” ማለት ነው)፣ ቁርባን ወይም የጌታ ማዕድ ተብሎ ሲጠራ ልትሰማ ትችላለህ። የጌታ እራት እርሱ ተላልፎ በተሰጠባት ምሽት በራሱ በኢየሱስ ለቤተክርስቲያን ተሰጥቶ ነበር።

ለ. በኢየሱስ ክርስቶስ የተመሰረተ

1. ማቴ. 26፡26-29

2. 1 ቆሮ. 11፡23-26

ሐ. ከቤተክርስቲያን የቀደሙ ዘመናት አንስቶ በመደበኛነት ይከበራል።

Made with FlippingBook - professional solution for displaying marketing and sales documents online