Theology of the Church, Amharic Student Workbook
5 4 /
የ ቤ ተ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሥ ነ - መ ለ ኮ ት
ሁሉም ቀደምት ማስረጃዎች... እንደሚያመለክተው የጥንታዊቷ ቤተክርስቲያን የአገልግሎት ተግባራት ምንም አይነት ቋሚ ቅደም ተከተል ባይኖራቸውም፣ በጌታ ቀን የሳምንታዊው አገልግሎት ዋና ክስተት የጌታ እራት ቅዱስ ቁርባን ነው።
~ R. G. Rayburn. “Worship in the Church.” Evangelical Dictionary of Theology. Walter A. Elwell, ed. Grand Rapids: Baker, 1996. p. 1193.
የጌታ እራት ለቤተክርስቲያን በጣም በተደጋጋሚ ማድረግ እንኳን ባይቻል ቢያንስ በሳምንት አንድ ጊዜ በጣም በጥሩ ሁኔታ ሊከበር ይችላል። . . . ያለ ቃሉ፣ ጸሎት፣ የጌታ እራት እና ለድሆች ገንዘብ ከመሰብሰብ ውጭ የሆነ ምንም ዓይነት የቤተክርስቲያን ስብሰባ እንደማይደረግ ሁል ጊዜ ልናስብ ይገባናል። ~ John Calvin. Institutes. 4.17.43-44. ሁለተኛው እያንዳንዱ ክርስቲያን በሚችለው መጠን ዘወትር ቁርባን መውሰድ ያለበት ምክንያት ማድረጉ የሚያስገኘው ጥቅም ብዙ ስለሆነ ነው። ... በዚህ ውስጥ የተሰጠን የእግዚአብሔር ጸጋ ኃጢአተኝነትን አስክዶን የኃጢአታችንን ይቅርታ አረጋግጦልናል። ሰውነታችን በእንጀራና በወይን እንደሚበረታ ነፍሳችንም በእነዚህ የክርስቶስ ሥጋና ደም ምልክቶች ትበረታለች። ይህ የነፍሳችን ምግብ ነው፡ ይህም ግዴታችንን ለመወጣት ጥንካሬን ይሰጠናል፤ ወደ ፍጽምናም ይመራናል። ስለዚህ ለክርስቶስ ግልጽ ትእዛዝ ልዩ አክብሮት ካለን፣ የኃጢያታችንን ይቅርታ ከፈለግን፣ ለማመን፣ እግዚአብሔርን ለመውደድ እና ለመታዘዝ ጥንካሬን ከፈለግን፣ የጌታን እራት የመውሰድን እድል ቸል ማለት የለብንም። እንግዲያውስ ጌታችን ካዘጋጀልን ግብዣ ፈጽሞ ፊታችንን መመለስ የለብንም። ለዚህ አላማ የእግዚአብሔር መልካም አቅርቦት የሚሰጠንን ማንኛውንም አጋጣሚ ቸል ማለት የለብንም። ትክክለኛው ህግ ይህ ነው፡ እግዚአብሔር እድል እንደሚሰጠን እንዲሁ ደግሞ መቀበል አለብን። እንግዲህ ሁሉ ተዘጋጅቶ ሳለ ከዚህ ቅዱስ ማዕድ የሚሄድ ሁሉ የኃጢአቱን ስርየትና የነፍሱን ማፅናትን ወይ ይህን ግዴታውን አልተረዳውም ወይም ታላቁ የአዳኙ ትእዛዝ ግድ የማይሰጠው ሰው ነው።
2
~ John Wesley. “Sermon 101: The Duty of Constant Communion.” The Works of John Wesley . Vol. 7-8. p. 148.
Made with FlippingBook - professional solution for displaying marketing and sales documents online