Theology of the Church, Amharic Student Workbook
/ 6 7
የ ቤ ተ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሥ ነ - መ ለ ኮ ት
አገልግሎት፣ እንዲሁም ቂጣውንና ወይኑን ለመቀደስ ወይም ለተቀደሱት ነገሮች በሙሉ ጥቅም ላይ ውሏል።
ለ. የጌታ እራት ዋና ልብ በክርስቶስ የፋሲካ በዓል ላይ ታይቷል። በፋሲካ እራት መገባደጃ ላይ፣ ኢየሱስ ቂጣውንና ጽዋውን አንሥቶ ለእግዚአብሔር የምስጋና መስዋዕት አድርጎ በላያቸው ላይ “አመሰገነ”። (1) ቂጣውን ቆርሶ ጽዋውን ለደቀ መዛሙርቱ አከፋፈለ፤ በቅደም ተከተል “እንካችሁ ብሉ” እና “ጨርሳችሁ ጠጡ” በማለት ጠየቃቸው። (2) ኢየሱስ ስለ ቂጣው፣ “ ይህ ስለ እናንተ የሚሰጠው ሥጋዬ ነው” እና ስለ ጽዋው “ይህ የቃል ኪዳን ደሜ ነው” ወይም ስለ ኃጢአት ስርየት “ይህ ስለናንተ በሚፈስሰው ደሜ የሚሆን አዲስ ኪዳን ነው” አለ።” (3) ኢየሱስም የዚህ በዓል ዓላማምን እንደሆነ ነገራቸው: እርሱም ለመታሰቢያው (እርሱን ለማስታወስ) ያደርጉት ዘንድ ነው።
2
ሐ. የጌታን እራት ተሰብስበን ስንወስድ፣ የመስቀል ላይ ስራውን እናስባለን፣ እርሱንም በደስታ ስናገለግለውና የቅርብ ዳግም ምጽዓቱን ስንጠባበቅ ጸጋውን እና ሰላሙን እንቀበላለን።
ሐ. እንደ እግዚአብሔር የቃል ኪዳን ማህበረሰብ አባላት በታዛዥነት አኗኗራችን፡-
1. እንደ አማኞች አንድ ላይ ሕይወታችን የአምልኮ ተግባር ሊሆን ይችላል፣ ከክርስቶስም ጋር ያለን ኅብረት እንደሆነው ሁሉ፣ ዕብ. 10፡24-25።
2. በቤተሰብ ሆነን በፍቅር እርስ በርሳችን ስንተሳሰብ እና ፈቃዱን ለማድረግ ስንጥር ሕዝቦቹ እንደመሆናችን መጠን ሕይወታችን ለእግዚአብሔር የአምልኮ ተግባር ሊሆን ይችላል።
ሀ. ሮሜ. 12.1
ለ. 1 ቆሮ. 10.31
Made with FlippingBook - professional solution for displaying marketing and sales documents online