Theology of the Church, Amharic Student Workbook
6 8 /
የ ቤ ተ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሥ ነ - መ ለ ኮ ት
ማጠቃለያ
» ቤተ ክርስቲያን እግዚአብሔርን የምታመልከው በብቸኛ ቅድስናው፣ ወሰን በሌለው ውበቱ፣ ወደር በሌለው ክብሩ እና አቻ ከሌለው ሥራው የተነሳ እግዚአብሔርን ለማክበር ነው። » የእግዚአብሔር አምልኮ ከሥላሴ አካላት ጋር ይዛመዳል፡ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል አማካኝነት በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ያህዌ አምላክን ብቻ እናመልካለን። » ቤተክርስቲያን እግዚአብሔርን የምታመልከው በምስጋና እና በውዳሴ እና ቃሉንና ምስጢራትን በሚያጎላ በስርዓተ ቅዳሴ፣ እንዲሁም እንደ ቃል ኪዳን ማህበረሰብ በመታዘዝ እና በአኗኗር ዘይቤዋ ነው። ከዚህ ቀጥሎ የቀረቡት ጥያቄዎች በዚህ በሁለተኛው ሴግመንት የቀረቡትን ሀሳቦች መለስ ብለህ ለመቃኘት እንዲረዱህ ነው፡፡ የዚህን ሴግመንት ዋና እውነቶች ስትለማመዱ፣ ከቤተክርስቲያን የአምልኮ ጥሪ ጋር የተያያዙትን መሰረታዊ ሀሳቦች መጨበጥ እና መረዳት ትፈልጋለህ። በተለይ ለእግዚአብሔር ከምናቀርበው አምልኮ በስተጀርባ ባለው ዓላማ ላይ አተኩር እና በአምልኮ ዓላማ እና በአምልኮ ተግባር መካከል ያለውን ግንኙነት ፈልግ። መልሶችህ ግልጽ እና አጭር ይሁኑ፣ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ደግሞ በቅዱሳት መጻሕፍት አስደግፍ! 1. በዚህ ሴግመንት መሠረት የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን እንደ አስፈላጊ ተግባር እና እውነተኛ ጥሪ በአምልኮ ውስጥ የምትሳተፍበት ማዕከላዊ እና ወሳኝ ምክንያት ምንድን ነው? 2. እግዚአብሔር ሁሉንም ነገር ለክብሩ፣ ለሞገሱ እና ለደስታው ማድረጉ ቤተክርስቲያን እግዚአብሔርን ለማምለክ ባላት ተነሳሽነት ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድረው እንዴት ነው? 3. ቤተክርስቲያን እግዚአብሔርን የምታመልከው ስለ ባሕሪውና ስለ ሥራው ግርማ ምክንያት የመሆኑን እውነታ አብራራ? እግዚአብሔርን እንድናመልከው የሚጠይቁንና ለአምልኮ የሚጠሩን የትኞቹ ባሕርያቱ ናቸው? 4. ቤተክርስቲያን ወደ እግዚአብሔር በአምልኮ የምትቀርበው በኢየሱስ ክርስቶስ ማንነት እና ስራ ብቻ እንደሆነ መረዳት አስፈላጊ የሆነው ለምንድነው? ይህ ካልሆነ በሌላ መንገድ ሊሆን ይችላል? መልስህን አስረዳ። 5. መንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያን እግዚአብሔርን በምስጋናዋ ለማክበር ስትፈልግ አምልኮዋን የሚያገንነው እና የሚያጎለብተው እንዴት ነው? ቤተክርስቲያን ለእግዚአብሔር ክብርን ስትሰጥ የመንፈስን ኃይል እንዴት ማግኘት ትችላለች? 6. ቤተክርስቲያን እግዚአብሔርን የምታመልክባቸው መንገዶች ምን ምን ናቸው: በታዛዥነቷ እና በአኗኗሯ? በስርዓተ ቅዳሴ፣ በተለይም ቃሉን በመስበክ እና ሥርዓተ ቁርባንን በማክበር? በአካላዊና በሙዚቃዊ ቅርጾችና አገላለጾች?
መሸጋገሪያ 2
2
የተማሪው ጥያቄዎች እና ምላሾች
Made with FlippingBook - professional solution for displaying marketing and sales documents online