Bible Interpretation, Amharic Mentor Guide
9 0 /
የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ-አፈታት
III. በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት አጠቃላይ መርሆችን ተግባራዊ አድርግ
ምሳሌዎችን ፈልግና ተከተላቸው
ሥነ-መለኮታዊ ውህደት አስፈላጊ ነው፤ ነገር ግን ጥሩ ያልሆነ ውህደት አሳሳች እና አደገኛ ነው። የኦርቶዶክስ እምነት ዋነኛ ክፍል ጥቅስን ከቁጥር፣ እውነትን ከእውነት ጋር በአግባቡ በማገናኘት ላይ እንደሚገኝ ብዙ ጊዜ ተመልክቷል። ይህ ሐሳብ ጥንቃቄ የተሞላበት ሥራ እንድንሠራ የሚጋብዝ ከመሆኑም በላይ፣ ጥንቃቄ የጎደለው ሥራ ከመሥራት እንድንቆጠብ ያስጠነቅቀናል። ሚዛናዊ መሆን ለጀማሪነት ፣ አንድን ምስጢራዊ ነጥብ ከተድበሰበሰ እና ከተነጠለ ምንባብ (ለምሳሌ. 1 ቆሮ. 15, 29) ላይ የተጠቀሰውን ሐሳብ በመጠቀም ቅዱሳት መጻህፍትን ለመተርጎም የሚያስችለንን መሠረታዊ መርህ ማዘጋጀት እንችላለን። ~ Donald A. Carson. New Bible Commentary: 21st Century Edition . (electronic ed. of the 4th ed.). Downers Grove, IL: InterVarsity Press, 1997.
ሀ. ትርጓሜ፡- ትግበራ ማለት በመንፈስ ቅዱስ ምሪት አማካኝነት የእግዚአብሔርን እውነት ለመቀበል የልብ ምላሽ ነው።
1. የልብ መግለጫ፡- ትግበራ አምኖ ከተቀበለ ሕሊና እና በቃሉ ውስጥ ላለው የእግዚአብሔር እውነት ዝግጁ ከሆነ ፈቃድ ጋር የተያያዘ ነው።
2. መንፈስ እንደመራ፡ ቃሉን የሚያነሳሳውና ልብን የሚያበራው ያው መንፈስ፣ መንፈስ ቅዱስ፣ ለእግዚአብሔር እውነት ምላሽ የመስጠት ፍላጎትንም ያቀጣጥላል።
2
ለ. ትግበራ አስተውሎ መለየትን ይጠይቃል።
1. መንፈስ ቅዱስ በክርስቲያናዊው ሕይወት ውስጥ በሁሉም እውነተኛ እንቅስቃሴዎች ውስጥ ድርሻ ይወስዳል፣ ዮሐንስ 15.26-27
2. ጥልቅ ዕይታ የጌታ ስጦታ ነው።
ሀ. መዝ. 119.33
ለ. ዮሐንስ 14: 26
ሐ. ያዕቆብ 1፡5
መ. 1 ዮሐንስ 2.
Made with FlippingBook flipbook maker