Bible Interpretation, Amharic Student Workbook
/ 1 0 7
የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ-አፈታት
መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሥነ-ጽሑፍ የመጽሐፍ ቅዱስ ዘውጎችን መተርጎም
ትምህርት 3
የትምህርቱ ዓላማዎች
ሃያል በሆነው በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ሰላም ለአንተ ይሁን ! የዚህን ትምህርት (ሞጁል) መጽሐፍ ካነበብክ፣ ካጠናህ፣ ውይይት ካካሄድክና ወደ ተግባር ከቀየርከው በኋላ የሚከተሉትን ማድረግ ትችላለህ:- • “ዘውግ” የሚለውን ቃል ፍቺ እና በመጽሐፍ ቅዱስ አተረጓጎም ውስጥ ያለውን ሚና ትለያለህ፣ ይህም ማለት እውነትን የሚያስተላልፍ እና በዚህ ቅፅ ህግጋት መሰረት መተርጎም ያለበት ልዩ የስነ-ጽሁፍ አይነት መሆኑን። • መጽሐፍ ቅዱስ ለሥነ ጽሑፍ ሕጎችና መርሆች ትኩረት የሚሰጥ መጽሐፍ መሆኑን፤ እንዲሁም እግዚአብሔር ቃሉን ለማስተላለፍ የሰውን የሥነ ጽሑፍ ስልቶች የተጠቀመበትን መንገድ መሠረታዊና ጠቃሚ የሆኑትን የቅዱሳት መጻሕፍት የዘውግ ጥናት መንተን፤ • ትረካ(ታሪካዊም ሆነ ምናባዊ)፣ ህግ (የህግ መጻሕፍት)፣ መልዕክቶች (ደብዳቤዎች)፣ ትንቢት፣ የጥበብ ሥነ-ጽሑፍ (ምሳሌያዊ አነጋገሮች፣ መነባንቦች፣ እንቆቅልሾች፣ ተረቶች፣ ምሳሌዎች፣ ወዘተ) እና ግጥሞችን ያካተተ አንዳንድ አስፈላጊ የሆኑት የመጽሐፍ ቅዱስ ዘውጎችን መዘርዘር፤ • የመጽሐፍ ቅዱስ ዘውጎችን ዓላማዎች ማቅረብ፣ ይህም አንድን ልዩ ፍላጎት ማሟላትን ጨምሮ፣ ስለ መሠረታዊ የሰው ልጅ ልምዳችን ያለንን ግንዛቤ የበለጠ ለማዳበር፣ እውነታውን እጅግ በተጨባጭ ሁኔታ ለመምሰል ያስችለናል፣ በመንፈስ መሪነት የመጽሐፍ ቅዱስ ደራሲያን ጥበብ ለማሳየት፣ እና የእግዚአብሔርን ምስጢር ባለጠግነት እና በዓለም ላይ ያለውን ሥራውን ለማሳየት። • የጸሐፊውን መነሻ ሀሳብ ለማወቅ፣ ነፍሳችንን ለማነጽ፣ ለሕይወት ያለንን አድናቆት ለማበልጸግ፣ ለተዝናኖት እና በምንመረምረው የሥነ ጽሑፍ ዓይነት ውስጥ የእግዚአብሔር ማንነት ስለሚበራልን ዘውግን በጥንቃቄ ለማጥናት ኃይልን እደሚያስገኝልን ትገነዘባለህ፡፡ • “የተለየ ሥነ-አፈታት” የሚለውን ቃል ማለትም፡ የመጽሐፍ ቅዱስ አጻጻፍ ቅርጾች እንድንተረጉም የሚያግዙን ህጎች እና ሂደቶች መጠቀም፤ ማለት ምን ማለት እንደሆነ ማብራራት • የመጽሐፍ ቅዱስ ትርክቶች እንደሚነግሩን፡- መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔርን ሥራ ዘገባ ማቅረቡ፣ የሥነ መለኮት ሁሉ ጭብጥ ከመጽሐፍ ቅዱስ መሆናቸው፣ ዘገባዎች የሚያመለክቱ ታሪኮች ታማኝ እና ትክክለኛ መሆናቸው፣ ታሪኮቹ በጥበባዊ ችሎታ እና ክህሎት መጻፋቸው እና ደርዝ ባለው መልኩ ማካተቱ የመጽሐፍ ቅዱስን ታሪክ ሥነ መለኮት ትርጉም እንዳለው ትገነዘባለህ፡፡
3
Made with FlippingBook - Online Brochure Maker