Bible Interpretation, Amharic Student Workbook

1 0 8 /

የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ-አፈታት

• የታሪክ ሥነ-መለኮት ቁልፍ ሀሳቦችን ማሳየት: እነዚህ ታሪኮች ከሥርዓተ ቁርባን ጋር ያስተዋውቁናል፣ ከእውነታዎች የበለጠ አስፈላጊ መሆናቸውን፣ ለክርስቲያን ማህበረሰብ መደበኛ መሆናቸውን፣ ክርስቲያናዊ ወጎች በታሪክ ተሻሽለው እራሳቸውን እንደሚገልጹ፣ እና ታሪኮቹም ቀድመው ማህበረሰቡን እንደሚያፈሩ፣ ተጠያቂነትን ያፈራሉ፣ እንዲሁም ስነ መለኮትን፣ የአምልኮ ሥርዓትን እና ቅዱስ ቁርባንን ያፈራሉ። ታሪክ ናቸው። • የታሪኩን አቀማመጥ፣ ገጸ-ባህሪያትን፣ የደራሲውን ምልከታ፣ ሴራ እና የታሪኩን ጭብጥ ጨምሮ በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ያሉትን አጠቃላይ የትረካ አካላት ማዘጋጀት እና ማቅረብ፤ • ትንቢትን እንደ መጽሐፍ ቅዱሳዊ የትርጓሜ ዘውግ እንዴት ስለ እግዚአብሔር እና ስለ ጽንፈ ዓለሙ እውነትን እንደሚያቀርብ፣ ከመንፈስ እንደሚፈስ እና ከእግዚአብሔር የተወሰነ የመገለጥ ዘዴ መሆኑን፣ በግል እና በጽሑፋዊ ሁነታዎች የሚገለጥ መሆኑን ጨምሮ አጠቃላይ መርሆችን ማብራራት ትችላለህ፣። • የአፖካሊፕቲክ/ነገረ ፍጻሜያዊ/ትንቢታዊ ጽሑፎችን እንደ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ዘውግ ፍቺ፣ ትርጉም፣ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያሉትን የአፖካሊፕስ ዓይነቶች (ማለትም፡- ዳንኤል እና ራዕይ)፣ ሁለቱንም ዋና ዋና የአይሁድ ነገረ ፍጻሜያዊ እና ጥሩ ይዘት ያላቸው መጽሐፍትን ማብራራት፤ • ለትንቢታዊ እና ነገረ ፍጻሜያዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ዘውጎች ሦስቱን የትርጓሜ መርሆች፡ - በኢየሱስ ክርስቶስ ማንነት ላይ ማተኮር፣ ትንቢታዊ መልዕክቶችን ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ጥሪ ማመላከት እና በክፋት፣ በመከራና በፍትሕ መጓደል ፊት የእግዚአብሔርን ሉዓላዊ ዓላማዎች ፍጻሜ በሚያመላክት መልኩ ማዘጋጀት፤ ና! የቃሉን ጥልቀት መርምር መዝ. 78.1-8 - “ሕዝቤ ሆይ፥ ሕጌን አድምጡ፤ ጆሮአችሁንም ወደ አፌ ቃል አዘንብሉ። አፌን በምሳሌ እከፍታለሁ፤ ከቀድሞ ጀምሮ፥ ያለውንም ተምሳሊት እናገራለሁ። የሰማነውንና ያውቅነውን፥ አባቶቻችንም የነገሩንን፥ ለሚመጣ ትውልድ ከልጆቻቸው አልሰወሩም። የእግዚአብሔርን ምስጋናና ኃይሉን ያደረገውንም ተኣምራት ተናገሩ። ለልጆቻቸው ያስታውቅ ዘንድ፥ ለአባቶቻችን ያዘዘውን ምስክር በያዕቆብ አቆመ፥ በእስራኤልም ሕግን ሠራ፤ የሚመጣ፥ ትውልድ የሚወለዱም ልጆች ያውቁ ዘንድ፥ ተነሥተው ለልጆቻቸው ይነግራሉ፤ ተስፋቸውን በእግዚአብሔር እንዲያደርጉ፥ የእግዚአብሔርንም ሥራ እንዳይረሱ፥ ትእዛዙንም እንዲጠብቁ፤ እንደ አባቶቻቸው እንዳይሆኑ፥ ጠማማና የምታስመርር ትውልድ፥ ልብዋን ያላቀናች ትውልድ፥ ነፍስዋ በእግዚአብሔር ዘንድ ያልታመነች፤” መጽሐፍ ቅዱስ በምስል፣ በዘይቤ፣ በምሳሌታዊ እና በታሪክ እንዲጻፍ የእግዚአብሔር ዓላማ ምንድን ነው? እግዚአብሔር ግለጽ በሆኑ/ፍቺ በማይፈልጉ ቋንቋ ብቻ ሳይሆን በምሳሌና በዘይቤያዊ አነጋገር የሚናገረን እና የሚጽፍልን ለምድነው? እኛን ለማሳሳት፣ ፈቃዱንና ቃሉን እንዳናውቅ/ለማወቅ አስቸጋሪ እንዲሆንብን ለማድረግ ፈልጎ/አስቦ ነው?

3

ጥሞና

Made with FlippingBook - Online Brochure Maker