Bible Interpretation, Amharic Student Workbook

/ 1 3 9

የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ-አፈታት

ሠ. የታሪኩ ጭብጥ የእግዚአብሔር መሠረታዊ ሥርዓቶችና እውነቶች) ምን እንደሆነ ልብ በል።

1. መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

ሀ. ስለ “እውነታው ያለው አመለካከት፣” (ዓለም ምን ይመስላል እና እኛ በውስጡ ማን ነን?

ለ. ስለ ሥነ ምግባር ያለው አመለካከት

ሐ. ስለ ዋጋ ያለው ግንዛቤ (የመጨረሻው ጉዳይ ምንድነው?

2. ስለ እግዚአብሔርና ስለ ራሳችን ምን እንማራለን?

3

የቅዱሳት መጻህፍት አንድነትና ልዩነት ባጭሩ የቅዱሳት መጻሕፍት አንድነትና ልዩነት እውቅና ሊሰጠውና በጥልቀት ሊታይ የሚገባው ጉዳይ ነው። የበለጠ የሊበራል ስኮላርሺፕ በልዩነት ላይ ያተኩራል ስለዚህ አንድነት ይጠፋል። የበለጠ ወግ አጥባቂ ስኮላርሺፕ በአንድነት ላይ ያተኮረ በመሆኑ ልዩነቱ ይጠፋል። የቅዱሳት መጻሕፍት አንድነት እውቅና ከሌለው ፣ ቀኖና ሙሉ በሙሉ በታሪክ እንዳደረገው ለክርስቲያናዊ እምነት እና ተግባር እንደ ሥልጣን መሠረት ሆኖ ሊሠራ አይችልም። እያንዳንዱን ጽሑፍ፣ መጽሐፍና ደራሲ በራሱ አገላለጽ ከመስማት የሚገኘውን ልዩነት አለማድነቅ፣ አንድ ሰው ቅዱሳት መጻሕፍትን በተሳሳተ መንገድ መተርጎም እና እግዚአብሔር በታሪክ ውስጥ በማንኛውም ጊዜ ለሕዝቡ ምን ሊናገር እንዳሰበ ላለማስተዋል ያጋልጣል። ከሥነ-መለኮት አኳያ፣ የቅዱሳት መጻሕፍት አንድነት ግለሰቦች ወይም ‘አብያተ ክርስቲያናት’ በሕጋዊ መንገድ ክርስቲያን ተብለው ሊጠሩ የማይችሉትን የአስተሳሰብ እና የባህሪ ገደቦችን ያሳያል። በሌላ በኩል፣ የቅዱሳት መጻሕፍት ልዩነት የትኛውም ክፍል ወይም የቤተ ክርስቲያን ትውፊት እውነት ላይ ብቸኛ ስልጣን እንደሌለው ያሳያል። አንዱ በጣም ሰፊ በሆነ ወይም ጠባብ በሆነ መንገድ ከማሰቡ የተነሳ ብቻ ኑፋቄን ሊለማመድ ይችላል! ~ C. L. Blomberg. “The Unity and Diversity of Scripture.” The New Dictionary of Biblical Theology. T. D. Alexander, ed. (electronic ed.). Downers Grove, IL: InterVarsity Press, 2001.

Made with FlippingBook - Online Brochure Maker