Bible Interpretation, Amharic Student Workbook
1 4 8 /
የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ-አፈታት
1. የእግዚአብሔር መንግሥት አገዛዝ ሁሉንም ዓለማዊ ተተኪዎች በመጨረሻ ያደቃል፣ ዳን. 2.44.
2. የእግዚአብሔር ሉዓላዊ ዓላማ በመጨረሻ በሁሉም የጽንፈ ዓለሙ ገጽታዎች ይፈጸማል፣ ሁሉም ለክብሩ እና ለስሙ፣ ዳን. 4፡34-37።
3. እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ሁሉ እንደ ሥራው፣ መልካምም ሆነ ክፉ፣ በመጨረሻ ይከፍላቸዋል፣ ራዕ. 22፡8-16።
ማጠቃለያ
» በመጽሐፍ ቅዱሳዊ ዘውጎች ጥናት ውስጥ፣ ምናልባት ሌሎች ዘውጎች የትረካን እና የትንቢትን ያህል ጎልተው የሚታዩ እና ለጥናት የሚጠቅሙ አይደሉም። » በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የተለያዩ የዘውግ ዓይነቶችን ሕጎች ስናገኝ፣ የእግዚአብሔርን እውነት በአስደናቂው ቃሉ ውስጥ ለማወቅ የቅርጹን ደንቦች በተሻለ ሁኔታ ለመረዳት እና ተግባራዊ ለማድረግ እንችላለን።
3
የሚከተሉት ጥያቄዎች የተነደፉት በሁለተኛው የቪዲዮ ሴግመንት ውስጥ ያለውን ይዘት ለመገምገም ለመርዳት ነው። በዚህ ክፍል የ“ልዩ ትርጓሜ”ን ሚና በሁለት የተለያዩ የሥነ ጽሑፍ ዓይነቶች ማለትም ትረካ እና ትንቢት ተመልክተናል። የትረካ ዘገባዎች የታሪክ ሥነ-መለኮት መሠረት ሆነው ያገለግላሉ፣ ትንቢት ስለ እግዚአብሔር እና ስለ ጽንፈ ዓለሙ በግል እና በጽሑፋዊ ሁነታዎች እውነትን ይሰጣል። ዘውጎችን በመተርጎም የተሻለ ስትሆን፣ በቃሉ መበልጸግ እና መታነጽ ይሆንልሃል፣ ቅዱሳት መጻሕፍትንም በኃይል እና ግልጽነት የማስተማር እና የመስበክ አቅምህ ያድጋል። የሁለቱም የትረካ እና የትንቢት ልዩ ትርጓሜዎች፣ የአፖካሊፕቲክ ጽሑፎችን ጨምሮ ማዕከላዊ ፅንሰ-ሀሳቦችን በጥንቃቄ በመመርመር የሚከተሉትን ጥያቄዎች መልስ። 1. “ልዩ ትርጓሜ” የሚለው ፍቺው ምንድን ነው? መመሪያዎቹና አሠራሮቹ የመጽሐፍ ቅዱስን የተለያዩ ሥነ-ጽሑፋዊ ቅርጾች እንድንተረጉም የሚረዱን እንዴት ነው? 2. ትረካ ምንድን ነው? በራሱ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥስ ምን ያህል ጎልቶ ይታያል? “ታሪካዊ” እና “ምናባዊ” በሆኑት የትረካ መንገዶች መካከል ያለው ልዩነት ምንድነው? 3. የትረካ ወይም የታሪክ ተመራማሪዎች በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ካሉት ትረካዎች ጋር እንዴት ይዛመዳሉ? ለታሪክ ሥነ-መለኮት ሀሳብ ቅርፅ እና ይዘት የሚሰጡትን አጠቃላይ ግምቶችን አሰላስል።
መሸጋገሪያ 2
የተማሪው ጥያቄዎች እና ምላሾች
Made with FlippingBook - Online Brochure Maker