Bible Interpretation, Amharic Student Workbook
/ 1 4 9
የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ-አፈታት
4. ከታሪክ የስነ-መለኮት ሊቃውንት ግምቶች ውስጥ፣ የመጽሐፍ ቅዱስን ታሪኮች፣ ታሪክ እና የእግዚአብሔር መገለጦችን በቁም ነገር ለመመልከት ለምንፈልግ ሁላችንም በጣም አስፈላጊ የሆነው የትኛው ነው ብለህ ታምናለህ? 5. የታሪክ አተረጓጎማችን እና እግዚአብሔር በመጽሐፍ ቅዱሳዊ ታሪክ ዘገባዎች ውስጥ በጸሐፊው አስተያየት የሚሰጠን ሐተታ እና ትርጉሙ ምን ግንኙነት አለው? መልስህን አስረዳ። 6. በዚህ ክፍል ውስጥ የተካተቱትን ስለ ታሪኮች፣ መጽሐፍ ቅዱስ እና ቤተክርስቲያን ቁልፍ ሀሳቦችን ዘርዝር። በመጽሐፍ ቅዱሳዊ አተረጓጎም ውስጥ የትረካን ሚና በቁም ነገር ለመውሰድ በምንፈልግበት ጊዜ ከቀረቡት ሃሳቦች ሁሉ፣ የትኛዎቹን ማወቅ በጣም አስፈላጊ ነው ብለህ ታምናለህ? መልስህን አስረዳ። 7. በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የትረካ አጠቃላይ ገጽታዎች ምንድናቸው፣ በሌሎች ልብ ወለዶች፣ አጫጭር ታሪኮች ወይም ሌሎች የሥነ ጽሑፍ ዓይነቶች ውስጥ ከተነገሩት ሌሎች ታሪኮች ጋር እንዴት ይዛመዳሉ? 8. ትንቢትን እንደ ዋና የቅዱሳት መጻሕፍት ዘውግ ግለጽ። ትንቢት ስለ እግዚአብሔር፣ ስለ አጽናፈ ዓለሙ እና በዓለም ላይ ስላለው ሥራ ካለን እውቀት ጋር የሚዛመድበት ሁኔታ እውነት ስለመሆኑ በምን እናውቃለን? 9. “አፖካሊፕቲክ ሥነ ጽሑፍ” ምንድን ነው? የዚህ የትንቢት ንዑስ ዘውግ የሚገኝባቸው የትኞቹ የመጽሐፍ ቅዱሳችን መጻሕፍት ናቸው? የአፖካሊፕቲክ ዘውግ ጥናት ውጤታማ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጓሜ ለማግኘት በጣም አስፈላጊ የሆነው ለምንድነው? 10. ሁለቱንም ትንቢቶችን እና አፖካሊፕቲክ የቅዱሳት መጻሕፍት ዘውጎችን በትክክል መተርጎም ከፈለግን የትኞቹ ሦስት መርሆዎች እና አመለካከቶች ጠቃሚ ናቸው? ይህ ትምህርት የሚያተኩረው በመጽሐፍ ቅዱሳዊ ትርጓሜ ውስጥ ባለው ሚና እና የዘውግ አጠቃቀሞች ላይ ነው። ከዚህ በታች ያሉት ፅንሰ-ሀሳቦች በልዩ ትርጓሜዎች ውስጥ ስለ ዘውጎች አስፈላጊነት በዚህ ክፍል የተሸፈኑትን ዋና ዋና ግንዛቤዎችን ያጠቃልላሉ። ³ “ዘውግ” የሚለው ቃል (ጃን-ራህ ተብሎ ይጠራል) የሚያመለክተው እውነትን የሚያስተላልፍ እና በዚያ ቅርፅ ህግጋት መሰረት መተርጎም ያለበት ልዩ የስነ-ጽሁፍ አይነት ነው። ³ መጽሐፍ ቅዱስን እንደ ዘውግ በመተርጎም ረገድ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መሠረታዊ እሳቤዎችን በጥንቃቄ መረዳት መጀመር አለበት፣ ይህም መጽሐፍ ቅዱስ ራሱ እንደ ሌሎች የሥነ ጽሑፍ ሥራዎች ሁሉ የሥነ ጽሑፍ ደንቦች እና መርሆዎች ትኩረት በመስጠት የተደራጀ እና የሚተዳደር የሥነ ጽሑፍ መጽሐፍ መሆኑን ያረጋግጣል፣ እንዲሁም እግዚአብሔር ቃሉን ለእኛ ለማስተላለፍ ዘውጎችን እና ሰብዓዊ ሥነ-ጽሑፋዊ ስልቶችን ተጠቅሟል።
3
ግንኙነት
የቁልፍ ጽንሰ ሐሳቦች ማጠቃለያ
Made with FlippingBook - Online Brochure Maker