Bible Interpretation, Amharic Student Workbook

1 5 2 /

የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ-አፈታት

* የመጽሐፍ ቅዱስን ታሪኮች እና ትንቢቶች በማጥናት ምን ያህል ጊዜ ታጠፋለህ? እነዚህ ሁለት ዘውጎች ከመጽሐፍ ቅዱሳዊ ይዘቶች ውስጥ አብዛኞቹን ያካተቱ ከመሆናቸው አንጻር፣ አሁን ባደረግከው የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ይህንን ነገር ችላ እያልክ ነው ወይስ ይበልጥ ትኩረት እያደረግህበት ነው? * የምታተኩርበት የተወሰነ የመጽሐፍ ቅዱስ ዘውግ አለ? ትኩረትህን በዚህ አይነት ዘውግ ላይ እንድታደርግ ያደረገህ ምክንያት ምንድነው - ለመረዳት የቀለለ ነው፣ የበለጠ አስደሳች ነው፣ ወይስ ሌላ ምክንያት? * ወንጌላትን እና በውስጣቸው ያሉትን ምሳሌዎች በማጥናት ምን ያህል ጊዜ ታጠፋለህ? “ትረካ እንዴት እንደሚሰራ” በተሻለ ሁኔታ ከተረዳህ በወንጌሎችና በሐዋርያት ሥራ እንዲሁም በሌሎች የታሪክ ዘገባዎች ላይ ብዙ ጊዜ ልታጠፋ እንደምትችል ታስባለህ? * በዚህ የታሪክ ሥነ-መለኮት ትምህርት ውስጥ የተካተቱትን አስተያየቶች ስንመለከት፣ የተጋነኑ ወይም ለአንተ እውነት ያልሆኑ የሚመስሉ ሐሳቦች አሉ? መልስህን አስረዳ። ከሆነ፣ ከምታምነው ነገር ጋር የበለጠ እንዲስማማ ሀሳቡን እንዴት እንደገና ትገልፃለህ? * ከዚህ በፊት የትንቢት እና አፖካሊፕቲክ መጻሕፍትን በጥልቀት አጥንተህ ታውቃለህ? በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንደዚህ ዓይነት ጽሑፎችን ከማጥናትህ በፊት ምን መደረግ አለበት - እነዚህን መጻሕፍት እንዴት ማጥናት እንዳለብህ በማወቅ ረገድ ክፍተቶችህ ምንድን ናቸው ? በጣም ብዙ ህጎች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያሉትን ጽሑፋዊ ዘውጎች ልዩነት (ማለትም፣ ግጥሞች፣ ንባብ፣ መዝሙሮች፣ ታሪኮች፣ ዘይቤዎች፣ ምሳሌያዊ ጽሑፎች፣ ትንቢት፣ ወዘተ.) በመመልከት አንዳንዶች በዘውግ ጥናት በጣም ተስፋ ይቆርጣሉ። ለምን እንደሆነ ልትረዳ ትችላለህ፤ ስለ ሁሉም ጥሩ ግንዛቤ ለማግኘት ሁሉንም የመጽሐፍ ቅዱስ ዘውጎች ለመማር በቂ ጊዜ ማሳለፍ የሚችል ማነው? እንደዚህ ያለው ተግባር ከባድ አይደለም? በአንድ የተወሰነ ዘውግ ላይ ብዙ አሥርተ ዓመታትን ያሳለፉ እና አሁንም ገና ምንም እንዳልገባቸው የሚናገሩ ምሁራን የሉም? በመጽሐፍ ቅዱስ ቋንቋዎችም ሆነ ዘውጎች ሊቅ ያልሆንን እኛ እነዚህን ደንቦች ለመጽሐፍ ቅዱስ ጥናታችን መሠረት አድርገን የምንጠቀመው እንዴት ነው? ለመጽሐፍ ቅዱስ ዘውግ ተኮር ዘዴ መከተላችን የእግዚአብሔር ቃል የሚሰጠንን አዲስ ግንዛቤ ለመቃረም ከመጀመራችን በፊት በጣም ብዙ ደንቦችን እንድናውቅ እና እንድንማር አያስገድደንም? ታሪኮች ለልጆች ስብከት በብዙ አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ ያለው የሕጻናት ስብከት ታሪክ የመንገሪያ ጊዜ ነው ማለት ይቻላል። ይህ የሚሆነው ያለ ፍላጎት ወይም ያለ ጠቀሜታ አይደለም። አብዛኛውን ጊዜ ልጆቹ እንዴት ማሰብ፣ መናገር፣ ማድረግና መምረጥ እንዳለባቸው ከሚያስተምረው ጋር የተያያዘ ጉዳይን ለመፍታት

3

ጥናቶች

1

2

Made with FlippingBook - Online Brochure Maker