Bible Interpretation, Amharic Student Workbook

1 6 0 /

የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ-አፈታት

• በመጽሐፍ ቅዱሳዊ ትርጓሜዎች ውስጥ የማጣቀሻ መርጃዎች ያላቸውን ሚና መግለጽ (ለምሳሌ፣ ርዕሳዊ መጽሐፍ ቅዱሶች፣ የማጣቀሻ መጽሐፍ ቅዱሶች፣ እና ርዕሳዊ መመሪያዎች እና ኮንኮርዳንሶች)፣ ለጥናት ያላቸውን ጠቀሜታ እና እንደነዚህ ያሉትን አጋዥ ማመሳከሪያዎች ስንጠቀም ልንገነዘባቸው የሚገቡንን አንዳንድ ዋና ዋና ጥንቃቄዎች ማሳየት ትችላለህ። • የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላትን፣ ኢንሳይክሎፔዲያዎችን፣ አትላሶችን እና የባሕልና የታሪክ መጽሐፎችን የምንጠቀምባቸውን ምክንያቶች መዘርዝር፤ እንዲሁም የእነዚህን ማመሳከሪያዎች ጥቅሞች መለየትና በእነዚህም ላይ ከመጠን በላይ መደገፍ በአተረጓጎማችን ላይ ምን ችግር ሊያስከትል እንደሚችል ማስጠንቀቅ ትችላለህ። • ከመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያዎች አጠቃቀም ጋር የተያያዙትን ትርጓሜዎች፣ ጥቅሞች እና ማስጠንቀቂያዎች መጥቀስ ትችላለህ። • ለትርጓሜያችን አጋዥ ሆነው የሚገኙትን ዋና ዋና የማብራሪያ ዓይነቶች መዘርዘር (ማለትም፣ የጥሞና፣ የአስተምህሮ፣ የጽሑፍ ጥናት እና የስብከት ዝግጅት)፣ እና ከአጠቃቀማቸው ጋር የተያያዙ ዋና ዋና ጥቅሞች እና ጥንቃቄዎችን መግለጽ ትችላለህ። • በሁለቱ የጽሁፉ አለም እና በእኛ ዘመናዊው ዓለም መካከል ያለውን ልዩነት ለማጥበብ የምናደርገውን ሙከራ ጨምሮ በመጽሐፍ ቅዱሳዊ አተረጓጎማችን ውስጥ ከመጽሐፍ ቅዱስ በተጨማሪ ሌላ አጋዥ ማመሳከሪያዎችን ለመጠቀም “ትክክለኛ አጠቃቀምን”ን ጠቅለል አድርገህ ማሳየት ትችላለህ። • የአጋዥ መሳሪያዎቹን ወሰን መግለጽ ትችላለህ፣ ይህም ማለት፣ በመጨረሻው ትንታኔ ላይ እንደሆነው ሁሉም ድምዳሜዎች ከቅዱሳት መጻሕፍት ትምህርቶች አንጻር በጥብቅ መፈተሽ እንዳለባቸው፤ እና ስለ ክርስቶስ ማንነት እና የቤዛነት ስራው የቅዱሳት መጻሕፍትን የሚቃረን ምንም ነገር ተቀባይነት እንደሌለው መግለጽ ትችላለህ። የከበረው መንፈስ ሐዋርያት 17: 10-12 - “ወዲያውም ወንድሞች ጳውሎስንና ሲላስን በሌሊት ወደ ቤርያ ሰደዱአቸው፥ በደረሱም ጊዜ ወደ አይሁድ ምኵራብ ገቡ፤ እነዚህም በተሰሎንቄ ከሚኖሩት ይልቅ ልበ ሰፊዎች ነበሩና፦ ነገሩ እንደዚሁ ይሆንን? ብለው ዕለት ዕለት መጻሕፍትን እየመረመሩ ቃሉን በሙሉ ፈቃድ ተቀበሉ። ስለዚህም ከእነርሱ ብዙ፥ ከግሪኮችም የከበሩት ሴቶችና ወንዶች ጥቂት ያይደሉ፥ አመኑ።” በቅዱሳት መጻሕፍት ትርጓሜ የእግዚአብሔርን ዓላማ እና ዕቅድ ለመረዳት በምናደርገው ጥረት፣ በጥቃቅንና ብዙም ጠቃሚ ባልሆኑ ጉዳዮች በቀላሉ መወሰድ፣ ከዋናው ይልቅ ዋና ባልሆነው ላይ ትኩረት ማድረግ እና እግዚአብሔር ለእኛ ሊናገረን የፈለገውን ነገር ልብ እና ነፍስ መሳት በጣም ቀላል ነው። በቅዱሳት መጻሕፍት ጥናት ላይ ካጠፋናናቸው ሰዓታት የተነሳ ያገኘነውን የእውቀት ጥልቀት በማሳየት ሌሎችን ለማስደመም መፈለግ አለብን? ሌሎችን ማረም የምንፈልገው የጽሑፉን መጀመሪያ ቋንቋ ትርጉም ባለመረዳታቸው ስላደረጉት የተሳሳተ ትርጓሜ ነው ወይስ እኛ ለማረም ደስተኛ የምንሆንባቸውን ታሪካዊ ወይም ሰዋሰዋዊ ስሕተት በመፈጸማቸው ነው? ሌሎች የሚያከብሩትና

4

ጥሞና

Made with FlippingBook - Online Brochure Maker