Bible Interpretation, Amharic Student Workbook

/ 1 6 1

የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ-አፈታት

ሊያማክሩት የሚፈልጉት አይነት ጥልቅ እውቀትና ማስተዋል ያለው ሰው በመሆን ጥሩ ስም ለማግኘት እንፈልጋለን? ስለ እግዚአብሔር ጥልቅ ነገሮች ባለን አስደናቂ ግንዛቤ አድማጮቻችንን ማስደነቅና የትምህርታችንን ጥልቀትና ብልሃት ሌሎች እንዲያስቡ ማድረግ እንፈልጋለን? ይህ ዓይነቱ የተዛባ ፍላጎት ሁልጊዜም በእግዚአብሔር ቃል ጥናታችንም ውስጥ ይገኛል፣ ቅዱሳት መጻሕፍትም ራሳቸው የእግዚአብሔርን ቃል እውቀት በተመለከተ ሊኖረን ስለሚገባው ትክክለኛ አመለካከት እና አካሄድ ፍንጭ መስጠታቸው ድንቅ ነው። በእውቀታችንም ሆነ በጽሑፍ ጥናታችን ሌሎችን ለመማረክ ወይም እነርሱን ለመጥቀም ከመፈለግ ይልቅ ከምንም በላይ ወደ ራሱ መጽሐፍ ቅዱስ መመለስ አለብን። በሌላ አነጋገር፣ ስለ ክርስቶስና ስለ መንግሥቱ የሚነሱ ጥያቄዎችን በሚመለከት፣ ለጥያቄዎቻችን መልስ ለማግኘት ወደ ራሱ ወደ መጽሐፍ ቅዱስ በመሄድ በአክብሮት ለመጽሐፍ ቅዱሳዊ ጥናት መገዛት አለብን። አድልኦን ማድረግ የለብንም ፣ የውሸት ወይም የማይረቡ አንጃዎችን መፍጠር የለብንም፣ የአምልኮ ስብዕናዎችን መከተል የለብንም ፣ ወይም በሌሎች ውጫዊ መልክ መደነቅ የለብንም። በመንፈሳዊ ጉዳዮች ሁሉ፣ ቅዱሳት መጻሕፍትን በራሳቸው በመመርመር መልሱን መፈለግ አለብን። ይህ አይነቱ ምሳሌ በሐዋርያት ሥራ 17፡1-9 ላይ የጳውሎስና ሲላስ በተሰሎንቄ ፍሬያማ የስብከትና የትምህርት አገልግሎት እንዳደረጉ የቤርያ ሰዎች ወሬውን መስማታቸው ታይቷል። በተሰሎንቄ ከሚገኙት ብዙ ቀናተኛ ግሪካውያንና ጥቂት መሪ ሴቶች በግልጽ ምላሽ ካገኙ በኋላ ጳውሎስና ሲላስ ትምህርታቸውን ባልተቀበሉ የአይሁድ አባላት ታድነዋል። ጳውሎስና ሲላስ ሊገኙ በማይችሉበት ጊዜ፣ ዓለምን ገለባብጠዋል፣ ረብሻም አነሳስተዋል በማለት ሕዝቡ ብስጭቱን በጄሰንና በሌሎቹ የጳውሎስ ወዳጆች ላይ አሰምቷል (17.6)። ጽሑፋችን የሚናገረው ስለ ኢየሱስ የተነገረውን የቃሉን አዋጅ በቤርያ በግልጽ ስለመቀበላቸው ነው፣ ሉቃስም በመንፈስ ቅዱስ ተነድቶ ሲናገር፣ ቤርያውያን በተሰሎንቄ ከነበሩት የበለጠ ክቡር መንፈስ እንደነበራቸው ይጠቁማል። የዚህ የቤሪያ ክቡር መንፈስ ባህሪ በትክክል ምን ነበር? በሐሥ 17፡11 ላይ በግልፅ ተጠቅሷል:- “እነዚህም በተሰሎንቄ ከሚኖሩት ይልቅ ልበ ሰፊዎች ነበሩና፦ ነገሩ እንደዚሁ ይሆንን? ብለው ዕለት ዕለት መጻሕፍትን እየመረመሩ ቃሉን በሙሉ ፈቃድ ተቀበሉ።” ቤርያውያን ስለ ኢየሱስ እና ስለ እግዚአብሔር መንግሥት ቃሉን በጉጉት ይማሩ ነበሩ። የእግዚአብሔርን ቃል በሙሉ ጉጉት፣ በረሃብና በከፍተኛ ፍላጎት ይቀበሉ ነበር፣ ስለ ቅዱሳት መጻሕፍትና ስለ ኢየሱስ የተናገሩትን የጳውሎስንና ሲላስን ቃል እንዳለ ከመቀበል ይልቅ “እነዚህ ነገሮች ትክክል መሆናቸውን ለማየት” በሚል አላማ በየዕለቱ የራሳቸውን ጥብቅ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ያደርጉ ነበር። እግዚአብሔር የእነርሱን ጥረት እንደጥርጣሬ ወይም አለመታዘዝ ሳይሆን፣ እንደ ክቡር መንፈስ፣ እንደሚጓጉ፣ እንደተራቡና እንደተመሰገኑ አድርጎ ተመለክቶታል። እዚህ ላይ ግልጽ የሆነው ነገር፣ በቅዱሳት መጻሕፍት ምስክርነት ካልተረጋገጠ በቀር ሐዋርያትም ሆኑ የትኛውም ባለሥልጣን ሊማከሩና ሊታመኑ እንደማይገባ ነው። ይህ ከመጽሐፍ ቅዱስ ትርጓሜ ተግባራችን ጋር እንዴት ይዛመዳል? አስደሳቹ ነገር፣ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ታላላቅ የመጽሐፍ ቅዱስ ምሑራን፣ በመጀመሪያዎቹ ቋንቋዎች ከተጻፉት ጀምሮ ሁሉም ዓይነት ርዕሰ ጉዳዮች በውስጡ እስከተካተቱበት ጥራዝ ድረስ የሕይወት ዘመናቸውን ሙሉ በመስጠት በማጥናት አሳልፈዋል። እነዚህም በሁሉም ቅጾች፣ በጽሑፍ፣ በዲጂታል፣ በበይነ መረብ፣ በድምጽ፣ በቪዲዮ - በመላው የቴክኖሎጂ ቅርጽ ቀርበዋል። ለእንደዚህ አይነት ስራውና እርዳታው የማይለካ

4

Made with FlippingBook - Online Brochure Maker