Bible Interpretation, Amharic Student Workbook

/ 1 7 1

የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ-አፈታት

ሐ. ለነጠላ ጽንሰ-ሀሳብ ብዙ ቃላት፡ እንግሊዘኛ ለፍቅር አንድ ቃል ብቻ ነው ያለው፣ ግሪክ ግን ብዙ አለው።

መ. የተለያዩ ቃላት ለጾታዎች: ብዙ ቋንቋዎች የወንድ፣ የሴትና የገለልተኛ ጾታ ቅርጾች አላቸው፣ እንግሊዘኛ ግን የለውም።

2. የቋንቋ እና የባህል ልዩነቶች ትርጓሜን አስፈላጊ ያደርገዋል።

ሀ. ግብርና፣ ጥንታዊ ተምሳሌትነት፡- አንዳንድ ባህሎች በግ አይተው አያውቁም ነገር ግን ዕብራውያን በግ እንደሚጠብቁ ሁሉ አሳማዎችን ይጠብቃሉ። ሲተረጉሙ ከባህላቸው የሆነን እንስሳ መጠቀም ምን ችግር አለው?

ለ. በአንዳንድ ባሕሎች ውስጥ የጽንሰ-ሐሳቦች አለመኖር: በአንዳንድ ባሕሎች ውሸት የሚናገሩ ሰዎች ብቻ እንዳልዋሹ እንደሚናገሩ ይታመናል። በሮሜ 9፡ 1 ላይ የጳውሎስን አባባል እንዴት ትተረጉመዋለህ? - “ብዙ ኀዘን የማያቋርጥም ጭንቀት በልቤ አለብኝ ስል በክርስቶስ ሆኜ እውነትን እናገራለሁ፤ አልዋሽምም፤ ሕሊናዬም በመንፈስ ቅዱስ ይመሰክርልኛል።”

4

ሐ. የትርጉም ተግዳሮቶች፡ ለቅዱሳት መጻሕፍት መልእክት እና ለተቀባዩ ባህል ቋንቋ እና ባህላዊ ደንቦች ታማኝ መሆን

1. ተርጓሚዎች በትርጉም ፍልስፍናቸው ውስጥ የተለያዩ ዘዴዎችን ይመርጣሉ።

ሀ. ቀጥተኛ ትርጉም - ትክክለኛ ቃላት (በተቻለ መጠን ቀጥተኛ ትርጉም)፣ በተቻለ መጠን ከመጀመሪያው ሰዋሰዋዊ መዋቅር ጋር ቅርብ

ለ. ተለዋዋጭ አቻነት - ትክክለኛውን ትርጉም ለመያዝ የሚችለውን ማንኛውንም ቃል መጠቀም

Made with FlippingBook - Online Brochure Maker