Bible Interpretation, Amharic Student Workbook
/ 1 9 7
የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ-አፈታት
ደቀመዛሙርትን ነፍስ የመንከባከብ ኃላፊነታቸውን ለመወጣት ከሌሎቹ ይልቅ አስፈላጊ የሆኑት የትኞቹ ናቸው ብለህ ታምናለህ? መልስህን አስረዳ። 3. መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትርጓሜዎችን ለማግኘት ከሚረዱት ዋነኞቹ ማመሳከሪያዎች መካከል አንዳንዶቹ ምንድን ናቸው? እነዚህ እርዳታዎች ከጽሑፉ ጋር በተያያዘ ምን እንድናደርግ ያስችሉናል? እነዚህ በተለይ የአንቀጹን ወይም የመጽሐፉን ትርጉም የበለጠ ለመረዳት የሚረዱን እንዴት ነው? በጥናታችን ላይ ስንጠቀምባቸው የትኞቹን ማስጠንቀቂያዎች ማስታወስ አለብን? 4. ስለ መጽሐፍ ቅዱሳዊው ዓለም ታሪክ፣ ባህል፣ ማኅበራዊ ልማዶች፣ ሕዝቦች እና የቦታ ሁኔታ ግንዛቤን በመስጠት ላይ የሚያተኮሩት ልዩ የማመሳከሪያ ጽሑፎች የትኞቹ ናቸው? እነዚህን መሳሪያዎች በጽሁፍ ጥናታችን ውስጥ የመጠቀም ዋና ጥቅሞች ምንድ ናቸው? በውስጣቸው ያሉትን ትክክለኛ የምርምር ውጤት ለመጠቀም በምንፈልግበት ጊዜ ምን ዓይነት ነገሮችን ማስታወስ አለብን? 5. በተለይ የመጽሐፉን ጸሐፊ፣ ጊዜ እና ሁኔታ ታሪክ እንዲሁም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስላሉት አንዳንድ የልዩ ቋንቋ አጠቃቀሞች (ለምሳሌ፣ ምልክት፣ ዘይቤ፣ ምሳሌያዊ ቋንቋ፣ ወዘተ) መረጃ ለማግኘት የሚረዱን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት አጋዥ መሳሪያዎች የትኞቹ ናቸው? እነዚህን መሳሪያዎች በጥናታችን ውስጥ በምንጠቀምበት ጊዜ ልንጠነቀቅባቸው የሚገቡት ጉዳዮች ምንድናቸው? 6. ከላይ ከተጠቀሱት ሌሎች በርካታ ማመሳከሪያዎች ጋር ሲነጻጸሩ የመጽሐፍ ቅዱስ ማብራሪያዎች ልዩ የማመሳከሪያ መሳሪያ የሆኑት ለምንድነው? በዛሬው ጊዜ ያሉት አራት ዋና ዋና የማብራሪያ ዓይነቶች የትኞቹ ናቸው? እያንዳንዱስ እንዴት ጥቅም ላይ ይውላል? 7. ማብራሪያዎች ጠቃሚና የተሟላ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችንና መጻሕፍትን በመረዳት ረገድ በጣም ጠቃሚ ቢሆኑም በምን መልኩ ነው ፈጽሞ ልንጠቀምባቸው የማይገባን? የትኛውም ጠቃሚና ጥሩ ተከታታይ ማብራሪያ ጽሑፉን በራሱ የማጥናትን ቦታ ሊወስድ ይችላል? አብራራ። 8. የመጽሐፍ ቅዱሳዊ ትርጓሜ መሳሪያዎችን “ትክክለኛ አጠቃቀም” በአንድ ነጠላ መግለጫ ማስቀመጥ ካለብዎህ ምን ልትል ትችላለህ? የቅዱሳት መጻሕፍትን ምሥክርነት የሚክድ ወይም የሚቃረን የትኛውንም ዓይነት ማመሳከሪያ አስተያየት መቀበል የሌለብን ለምንድነው? አብራራ። 9. መጽሐፍ ቅዱስ “በክርስቶስ ኢየሱስ በማመን ለመዳን ጥበበኞች እንድንሆን” ካለው ዓላማ አንጻር (2ጢሞ. 3፡15) ሁሉንም መሳሪያዎች በምንጠቀምበት ጊዜ ቅዱሳት መጻሕፍት ስለ ክርስቶስ ማንነት እና ስለ ቤዛነቱ ሥራ የሚሰጡትን ግልጽ ምስክርነት የሚያጠራጥር ምንም ነገር ተቀባይነት ሊኖረው የማይገባው ለምንድነው? አብራራ።
4
Made with FlippingBook - Online Brochure Maker