Bible Interpretation, Amharic Student Workbook

2 0 4 /

የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ-አፈታት

እነዚህ መሳሪያዎች የጥንቱን ዓለም በተሻለ ሁኔታ ለመረዳት የሚረዱባቸውን መንገዶች መረዳት፣ በዚህ ዓለም ውስጥ የተሻለ የእግዚአብሔር ቃል አገልጋይ እንድትሆን ያደርግሃል። በእግዚአብሔር ቃል ልክ ሁሉንም የአገልግሎትህን አቅጣጫ የሚነካ ነገር የለም። ግባችን ጳውሎስ ለጢሞቴዎስ በ2ኛ ጢሞ. 4፡1-2 ከተናገረው የጌታ ቃል ጋር መስማማት ይኖርበታል፡- “በእግዚአብሔር ፊት በሕያዋንና በሙታንም ሊፈርድ ባለው በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ፊት፥ በመገለጡና በመንግሥቱም እመክርሃለሁ፤ ቃሉን ስበክ፥ በጊዜውም አለጊዜውም ጽና፥ ፈጽመህ እየታገሥህና እያስተማርህ፥ ዝለፍና ገሥጽ ምከርም።” በእግዚአብሔር ቃል ራሳቸውን የሚገሥጹ፣ ቦታና ሁኔታ ምንም ይሁን ምን እግዚአብሔር በሚመራው በማንኛውም ጊዜ ለሌሎች ለመስበክ፣ ለማስተማር፣ ለመናገር፣ ለመምከር እና ለመጸለይ ዝግጁ በሚሆኑ የእግዚአብሔር ወንዶች ወይም ሴቶች ዘንድ ምንም የሚባክን ነገር የለም። ይህ ህልማችን እና ተልዕኮአችን ነው። አሁን አንተ እና መምህርህ በተስማማችሁት መልኩ በዚህ ሞጁል ውስጥ የተማርከውን ግንዛቤ በተግባራዊ መንገድ ለሌሎች ለማካፈል እድሉ አለህ። አሁን አስፈላጊው ነገር በዚህ ሞጁል ውስጥ የተማርከውን እና የተገበርካቸውን የበለጸጉ ግንዛቤዎች የምታካፍልበት ቦታ መፈለግ ነው - ከቤተሰብህ አባላት ጋር፣ በቤተክርስቲያንህ ውስጥ ባለ ቦታ፣ በስራህ ቦታ ወይም እግዚአብሔር በሚመራህ የትኛውም ቦታ ሊሆን ይችላል። ትኩረት ልትሰጥበት የሚያስፈልገው ነገር ይህ ትምህርት ከህይወትህ፣ ከስራህ እና ከአገልግሎትህ ጋር እንዴት እንደሚዛመድ ነው። የሚኒስትሪ ፕሮጀክቱ የተነደፈው ለዚህ ነው፣ በሚቀጥሉት ቀናት እነዚህን ግንዛቤዎች በእውነተኛ ህይወት እና አገልግሎት አከባቢዎችህ ውስጥ ለማካፈል እድሉን ታገኛለህ። በፕሮጀክትህ ውስጥ ያገኘኸውን ግንዛቤ ለሌሎች ስታካፍል እግዚአብሔር እንዲመራህና ማስተዋል እንዲሰጥህ ጸልይ። በዚህ የሞጁሉ የመጨረሻው ትምህርት ፣ ልብህን በጌታ ፊት ፈልግ - የመንፈስ ቅዱስን ምሪት እና ምላሽ የምትፈልግበት ቀሪ ጉዳዮች ፣ ሰዎች ፣ ሁኔታዎች ወይም ዕድሎች አሉ? በዚህ ትምህርት ውስጥ ስለ ድሆች እና ስለእነሱ ሃላፊነት መለወጥ ፣ መማር ፣ ማቆም ፣ መጀመር የሚፈልጉህ አንዳንድ ነገሮች አሉ? በዚህ ትምህርት ውስጥ ምልጃ እና ጸሎት እንደሚያስፈልገው እግዚአብሔር በልብህ ላይ ያስቀመጠው ለየት ያሉ ጉዳዮች ወይም ሰዎች አሉ? ጌታ የሚነግርህን ማንኛውንም ነገር ፣ ጥበብን ፣ ጥንካሬን እና ቃሉን በሕይወትህ እና በአገልግሎትህ ላይ ተግባራዊ ለማድረግ በእሱ በመተማመን ለራስህ እና ለባልንጀሮችህ ለመጸለይ አስፈላጊውን ጊዜ ውሰድ፡፡ አሁን በዚህ ሞጁል መጨረሻ ላይ ሆነህ በዚህ ትምህርት በጥናትህ ምክንያት ጸሎት የሚያስፈልጋቸው ቀሪ ጉዳዮች፣ ሰዎች፣ ሁኔታዎች ወይም እድሎች መኖራቸውን ወይም አለመኖራቸውን አስብ። በእነዚህ ጥናቶች ምክንያት በህይወትህ ሊያያቸው የሚፈልጋቸውን ማናቸውንም ትግበራዎች ወይም ለውጦች ወደ አእምሮህ እንዲያመጣ ጌታ መንፈስ ቅዱስን ጠይቀው፤ ጊዜም ወስደህ ጸሎት በሚያስፈልጋቸው ጉዳይ ላይ ከባልደረቦችህ ጋር ጸልይ። ይህን አስታውስ፣ ጸሎት ጌታችን እንድንለወጥና እንድናድግ የሚፈልጋቸውን የህይወታችን ክፍሎች በልበ ሙሉነት እና በድፍረት እንድንከታተል አስፈላጊውን ድጋፍ ይሰጠናል።

የአገልግሎት ግንኙነቶች

4

ምክር እና ጸሎት

Made with FlippingBook - Online Brochure Maker