Bible Interpretation, Amharic Student Workbook
/ 2 0 5
የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ-አፈታት
ምደባዎች
የቤት ስራ የለም
የቃል ጥናት ጥቅስ
የቤት ስራ የለም
የንባብ መልመጃ
አሁን የሚኒስትሪ ፕሮጀክትህ እና የኤክሴጀሲስ ፕሮጀክትህ በአስተማሪህ ተገምግሞና ተወስኖ ተቀባይነት ሊኖረው ይገባል፡፡ የተሰጡትን ሥራዎች በጊዜው ማስረከብ ትችል ዘንድ አስቀድመህ ማቀድህን አረጋግጥ።
ሌሎች የቤት ስራዎች
የማጠቃለያ ፈተና ማስታወቂያ
የመጨረሻው በቤት የሚሰራ ፈተና ይሆናል ፤ ከመጀመሪያዎቹ ሶስት ፈተናዎች የተወሰዱ ጥያቄዎችን ፣ ከዚህ ትምህርት የተገኙ አዳዲስ ጥያቄዎችን እና አጫጭር ምላሾችን የሚጠይቁ የጹሑፍ ጥያቄዎችንም ያጠቃልላል ፡፡ እንዲሁም በፈተናው ላይ ለትምህርቱ የተሰጡትን የቃል ጥናት ጥቅሶች በማንበብ ወይም በመፃፍ ላይ መዘጋጀት አለብህ፡፡ ፈተናህን ስታጠናቅቅ እባክህ ለመምህርህ በማሳወቅ ቅጅህን ማግኘቱን አረጋግጥ። ማስታወሻ - የመጨረሻውን ፈተና ካልወሰድክ እና ለአስተማሪህ የተሰጡትን የቤት ስራዎች ሁሉ (የሚኒስትሪ ኘሮጀክት ፣ የኤክሴጀሲስ ፕሮጀክት እና የመጨረሻ ፈተና) ባግባቡ ካላጠናቀቅህ በዚህ ሞጁል የሚኖርህን አጠቃላይ ውጤት ማስላት አይቻልም። በዚህ ትምህርት ውስጥ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጓሜያችንን ሊያሳድጉ የምንችልባቸውን መሳሪያዎች ተመልክተናል። የሕያው እግዚአብሔርን ዘላለማዊ ቃል በህይወታችን ተግባራዊ ለማድረግ የመጽሐፍ ቅዱስን ትርጓሜ አስፈላጊነት እና የልባችንን፣ የአዕምሮአችንን እና የፈቃዳችንን ዝግጅት ተመልክተናል። የመጽሐፍ ቅዱስን እስትንፋሰ እግዚአብሔርነት ጽንሰ ሃሳብ እና የዘመናችንን የመጽሐፍ ቅዱስ ምሁራዊ ምልከታዎች መርምረናል፣ እንዲሁም የእግዚአብሔር ቃል እንዴት በእግዚአብሔር መንፈስ አነሳሽነት እንደተጻፈ፣ ጸሐፊዎቹም በመንፈስ ቅዱስ ተመርተው የጻፏቸው ቅዱሳት መጻሕፍት በመሆናቸው እስትንፋሰ እግዚአብሔር መሆናቸውን ተመልክተናል። የሶስት ደረጃ ሞዴላችን የመጽሐፍ ቅዱስን ትርጉም በራሱ አውድ ለመረዳት፣ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መርሆችን ለማውጣት እና ትርጉሙን በተጨባጭ በመንፈስ መሪነትና አጋዥነት በሕይወታችን ውስጥ ተግባራዊ ለማድረግ ውጤታማ ሞዴል ሰጥቶናል። ከእነዚህ ግንዛቤዎች በተጨማሪ በመጽሐፍ ቅዱስ ትርጓሜ ውስጥ የዘውግ ጥናትን አስፈላጊነት ገለጸናል፣ በተጨማሪም በመጽሐፍ ቅዱስ ትርጓሜ ውስጥ የትረካ እና የትንቢትን አስፈላጊነት ተመልክተናል። በመጨረሻም፣ በጥንታዊው ጽሑፍ ላይ ባለን ግንዛቤና በራሳችን አተገባበር መካከል ያለውን ርቀት ለማስተካከል የሚረዱትን መሠረታዊም ሆነ ሌሎች መሣሪያዎችን መርምረናል። ምንም አይነት ዘዴዎች ወይም መሳሪያዎች ብንጠቀምም፣ የራሳችንን የተሳለጠ፣ በጸሎት እና በመታዘዝዝ የሆነን የእግዚአብሔር ቃል ጥናታችንን ምንም ነገር ሊተካው አይችልም። ከመንፈስ እርዳታ እና
4
ስለዚህ ትምህርት (ሞጁል) የመጨረሻ ቃል
Made with FlippingBook - Online Brochure Maker