Bible Interpretation, Amharic Student Workbook
4 6 /
የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ-አፈታት
የሚከተሉት ጥያቄዎች በሁለተኛው የቪዲዮ ክፍል ውስጥ ያለውን ሐሳብ እንድትገመግም ለመርዳት ታስበው የተዘጋጁ ናቸው። የመጽሐፍ ቅዱስን አመጣጥ፣ ሥልጣንና መንፈስ አነሳሽነት በተመለከተ የሚነሱ ጥያቄዎች የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጓሜዎች ሁሉ ዋነኛ ክፍል ናቸው። የመጽሐፍ ቅዱስን መለኮታዊ አመጣጥና ሰዋዊ ደራሲነት በተመለከተ ያለውን ጥያቄ እስካልፈታነው ድረስ የመጽሐፍ ቅዱስን ትርጓሜ በተመለከተ ያለንን አተረጓጎም መግለጽ አንችልም። ዘመናዊው የመጽሐፍ ቅዱስ ትችት መለኮታዊና ሰዋዊ ናቸው በሚሉት መካከል ያለውን ትክክለኛ ግንኙነት ለመግለጽ ይጥራል። ከታች ባሉት ጥያቄዎች ላይ አብራችሁ ስትወያዩ በጽሑፉ ላይ የተጠቀሱትን ዋና ዋና ሐሳቦች ስትገመግሙ የራስህን አመለካከት ግልጽ ለማድረግ ሞክር። የሚከተሉትን ጥያቄዎች በጥንቃቄ አንብብ፤ እና ቅዱሳት መጻሕፍት ከሚያስተምሩት ትምህርት አንጻር ለእነዚህ ጥያቄዎች መልስ ለማግኘት ሞክር። 1. ቅዱሳት መጻህፍት በእግዚአብሔር መንፈስ መሪነት የተጻፉ ናቸው የሚሉ ቢያንስ ሦስት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን ዘርዝር። መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል ነው ሲባል ምን ማለት ነው? በ2ኛ ጴጥሮስ ላይ የሚገኘውን የቅዱሳት መጻሕፍት ጥቅሶች የግል ትርጓሜ እንዳላቸው የሚገልጸውን ነገር እንዴት ትረዳዋለህ? (2 ጴጥ. 1.19-21)? 2. ሜካኒካል ወይም ዲክቴሽን ቲዎሪ ምንድን ነው? ምንስ ይዟል? 3. የመጽሐፍ ቅዱስን እስትንፋሰ እግዚአብሔርነት የሚገልጸውን ኢንቲዩሽን ወይም ናቹራል ቲዎሪ አብራራ። መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ራሱ ከሚናገረው ነገር አንጻር ይህን ቲዎሪ እንዴት ልንረዳው ይገባል? 4. የመጽሐፍ ቅዱስ እስትንፋሰ እግዚአብሔርነት ኢሉሚኔሽን ቲዎሪ ዋና ዋና ገጽታዎች ምንድን ናቸው? ቅዱሳት መጻሕፍት ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊዎች ስጦታ እና ስለ መጽሐፍ ቅዱስ መለኮታዊነት ለሚነሳው ጥያቄ መልስ የሚሰጡት እንዴት ነው? 5. ዲግሪስ ኦፍ ኢንስፓየር ቲዎሪ ስለ እግዚአብሔር ቃል ተፈጥሮ ከሚገልጸው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ጋር እንዴት ይስማማል? 6. ቨርባል/ፕሌነሪ ቲዎሪ ከተሰኘው የመጽሐፍ ቅዱስ አተረጓጐም ጋር የተያያዙ ዋና ዋና ፅንሰ ሀሳቦችን ዘርዝር። ይህ ቲዎሪ ከሌሎቹ በላቀ ሁኔታ በመጽሐፍ ቅዱስ አመጣጥና ሥልጣን ውስጥ ስላለው መለኮታዊና ሰዋዊ ግንኙነት ግልጽ መልስ የሚሰጠን ለምንድን ነው? 7. የዘመናዊው የመጽሐፍ ቅዱስ ትችት ዓላማ ምንድን ነው? ይህስ አላማ ተጨባጭ ነው? መልስህን አብራራ። 8. ከመለኮታዊ ክስተት አንስቶ እስከ ቅዱሳን ጽሑፎች ቅጂዎች ድረስ ያለውን ሂደት የሚከታተሉትን የተለያዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ትችት ንዑስ ክፍሎችን ጠቅለል አድርገህ ግለጽ። “ከፍተኛ” ትችትና “ዝቅተኛ” ትችት የሚለያዩት እንዴት ነው? ከእነዚህ ዘርፎች ጋር የተያያዙት ችግሮችና ጠቀሜታዎች ምንድናቸው?
መሸጋገሪያ 2
የተማሪዎች ጥያቄዎችና መልሶች
1
Made with FlippingBook - Online Brochure Maker