Bible Interpretation, Amharic Student Workbook
4 8 /
የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ-አፈታት
ከዚህ ቀጥሎ የቀረቡት ሐሳቦች ስለ ቅዱሳት መጻህፍት አመጣጥ፣ ሥልጣንና በመንፈስ አነሳሽነት የተጻፉ ስለመሆናቸው በሚገልጸው በዚህ ትምህርት ላይ የተወያየንባቸውንና ያሰላሰልናቸውን ወሳኝ እውነቶች ጠቅለል አድርገው ይገልጻሉ። መጽሐፍ ቅዱስን ለመረዳት የሚያስችለንን የራሳችንን የአረዳድ ዘዴ በጥንቃቄና በምክንያታዊነት ከመዘርጋታችን በፊት ቅዱሳን ጽሑፎች የእግዚአብሔር ቃል መሆናቸውንና በመንፈስ አነሳሽነት የተጻፉት መልእክቶች ተገቢውንና የሚጠይቀውን ዓይነት ትኩረት፣ አክብሮትና ጥልቅ ጥናት ሊሰጣቸው እንደሚገባ ሙሉ በሙሉ መተማመን ይኖርብናል። ከዚህ በታች የተዘረዘሩት እውነቶች በጥናትህ ውስጥ የተካተቱትን ነጥቦች ለመገምገም ጥሩ አጋጣሚ ይሰጡሃል። ³ ስነ አፈታት በትርጓሜ ላይ፣ በተለይም በምንባቦች ትርጓሜ ላይ የሚያተኩር የጥናት እና የእውቀት ዘርፍ ነው። የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጓሜዎች በተለይ መጽሐፍ ቅዱስን ለመተርጎም በሚያስችሉ ዘዴዎችና ሳይንስ ላይ ያተኩራሉ። ³ መጽሐፍ ቅዱስን እንደ መለኮታዊም ሆነ እንደ ሰዋዊ መጽሐፍ መተርጎም ያስፈልጋል፤ እንዲሁም የመጽሐፍ ቅዱስን ምንነት ሙሉ በሙሉ ለመረዳት መለኮታዊም ሆነ ሰዋዊ ባሕርያትን መገንዘብ ያስፈልጋል። ³ ስለ ቅዱሳት መጻሕፍት መለኮታዊ አመጣጥ፣ ቅዱሳት መጻሕፍትን ስለመተርጎም፣ ሂደታዊ የመገለጥ ሀሳብ፣ በክርስቶስ ላይ ያተኮረ የመጽሐፍ ቅዱስ ተፈጥሮ እና የእግዚአብሔርን ቃል ለመረዳት የመንፈስ ቅዱስ አስፈላጊነት ጨምሮ ስለ ቅዱሳት መጻሕፍት ተፈጥሮ ኦርቶዶክሳዊ ክርስቲያኖች ከመጀመሪያው አንስቶ ያመኑባቸውን ወሳኝ ቅድመ-ሁኔታዎችን አስቀምጠዋል። ³ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጓሜ የሦስት ደረጃ ሞዴል በሥነ ጽሑፉ ዓለም እና በዘመናዊው ዓለም መካከል ያለውን ታሪካዊ እና የቋንቋ ልዩነት በቁም ነገር ለመውሰድ የሚፈልግ ሲሆን መልእክቱን ከመጀመሪያው ሁኔታ አንጻር ለመረዳት ፣ ከመጽሐፉ የመጽሐፍ ቅዱስ መርሆችን ለማግኘት እና በመጨረሻም የቅዱሳት መጻሕፍትን ትርጉም በሕይወታችን ውስጥ ተግባራዊ ለማድረግ ጥረቶችን ማድረግን ያካትታል ። ³ የእግዚአብሔርን ቃል በትክክል ለመተርጎም ልባችንን፣ አእምሯችንንና ፈቃዳችንን በማዘጋጀት በትሕትናና በጥንቃቄ ማጥናት፣ በጥንቃቄ መመርመርና ከልብ መታዘዝ ይኖርብናል፤ ይህም ለእግዚአብሔር ክብርን ያመጣል። ³ ከመጽሐፍ ቅዱስ አንጻር እንደ ትጉ ሰራተኛ በትህትና እና በጸሎት፣ በትጋት እና በቆራጥነት እና ጥብቅ ተሳትፎ ልባችንን ማዘጋጀት አለብን። መጽሐፍ ቅዱስን በጥንቃቄ በመመርመርና ማስረጃዎችን በጥንቃቄ በመመዘን ቃሉን በመስማት ብቻ ሳይሆን በመታዘዝ ፈቃዳችንን ማዘጋጀት፣ እንዲሁም ጥበብ የሚገኘው ቃሉን በማሰላሰል ብቻ ሳይሆን ለእሱ ምላሽ በመስጠት እንደሆነ የሚገልጸውን እውነት መቀበል ይኖርብናል። ³ ቅዱሳት መጻሕፍት በግልጽ እና በድፍረት መጽሐፍ ቅዱስ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል እና አሠራር በእግዚአብሔር መንፈስ መሪነት “እስትንፋሰ እግዚአብሔር” እንደሆነ ይናገራሉ። መጽሐፍ ቅዱስ በሰዎች ደራሲነት እና በመለኮታዊ አነሳሽነት የተጻፈ መጽሐፍ ነው፣ ነገር
1
Made with FlippingBook - Online Brochure Maker