Bible Interpretation, Amharic Student Workbook
/ 4 9
የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ-አፈታት
ግን የትኛውም ቅዱስ መጽሐፍ በግለሰብ ፈቃድ የተተረጎመ አይደለም፣ ነገር ግን ደራሲዎቹ በመንፈስ ቅዱስ “ተነድተዋል”። ³ ቅዱሳት ጽሑፎችን የጻፉት ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተመርተው የተጻፉ መሆናቸውን የሚያረጋግጡት አምስት ዋና ዋና የመንፈስ አነሳሽነት ንድፈ ሐሳቦች ናቸው። እነዚህም ሜካኒካል ወይም ዲክቴሽን ቲዎሪ፣ ኢንቱይሽን ወይም ናቹራል ቲዎሪ፣ የኢሉሚኔሽን ቲዎሪ፣ ዘ ዲግሪስ ኦፍ ኢንስፓየሬሽን ቲዎሪ እና ቨርባል/ፕሌነሪ ቲዎሪ ይገኙበታል። ቨርባል/ ፕሌነሪ ቲዎሪ፣ ጸሐፊው የመረጣቸውን ቃላት ጨምሮ የቅዱሳት መጻሕፍቱ ሙሉ ጽሑፍ የእግዚአብሔር መሪነትና ምርጫ ውጤት ነው የሚል ነው። ³ በዘመናችን ያሉ የመጽሐፍ ቅዱስ ተንታኞች የመጽሐፍ ቅዱስን አመጣጥ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከተጠቀሱት የመጀመሪያዎቹ ክስተቶች በመነሳት በመጽሐፍ ቅዱስ ቅጂዎች ውስጥ ከተመዘገቡት ክስተቶች ጋር ለማገናኘት ይጥራሉ። ከቁጥጥር ክስተት ጀምሮ የእግዚአብሔርን መልእክት ከድርጊቱ ክዋኔ አንስቶ ዛሬ እስካለን የቅዱሳት መጻሕፍት ትርጉም ድረስ ለመከታተል ይሞክራል ። ³ የዘመናዊው የመጽሐፍ ቅዱስ ትችት ዋና ዋና ክፍሎች የቅርጽ ትችት (የቃል ወግ መከታተል)፣ የመነሻ ትችት (የመጀመሪያውን የጽሑፍ ምንጮች መፈለግ) ፣ የቋንቋ ትችት (ቋንቋ ፣ ቃላት እና ሰዋስው) ፣ ጽሑፋዊ ትችት (የጽሑፎች ቅጂዎች) ፣ የሥነ-ጽሑፍ ትችት (የሥነ-ጽሑፍ ህጎች) ፣ ቀኖናዊ ትችት (መጽሐፎች እንዴት እንደተመረጡ)፣ የአርትዖት ትችት (የደራሲዎቹ ዓላማዎች) ፣ ታሪካዊ ትችት (ታሪክ እና ባህል) ፣ እንዲሁም የትርጉም ጥናቶችን ያካትታል። በጥንቃቄና በዝግታ ማሰላሰል እና ማስተዋልን ተግባራዊ ማድረግህ እንደ ክርስቲያን መሪ ያለማቋረጥ እንድታድግ ቁልፍ ሚና ይጫወታል። በዚህ የትምህርታችን ክፍል ውስጥ ስለ ቅዱሳት መጻሕፍት አመጣጥና ሥልጣን በአእምሮህ ውስጥ ለሚነሱ ልዩ ጥያቄዎች ከክፍል ጓደኞችህ ጋር የምትወያይበት ጊዜ አሁን ነው። የቅዱሳት መጻሕፍት እስትንፋሰ እግዚአብሔርነት ጽንሰ-ሐሳብ አንተ በክርስቶስ ባለህ እድገት እና የተስፋ ቃላቶቹን በአገልግሎትህ ላይ ያለህን የማወጅ ችሎታ ማዕከል ያደረገ ላይ ነው። እንግዲህ እስካሁን ካጠናሃቸው ነገሮች አንጻር ወደ አእምሮህ የሚመጡትን ጥያቄዎች አስብና ከሌሎች ጋር አብራችሁ ተወያዩባቸው። ከዚህ በታች የቀረቡት ጥያቄዎች የአንተን ጥያቄዎች፣ ምልከታዎችና ተግዳሮቶች ሊዳስሱልህ ይችላሉ:- * እያንዳንዱ ክርስቲያን የመጽሐፍ ቅዱስን ትርጉም ለመረዳት በሚጥርበት ጊዜ አንድ የሆነ ዓይነት የ”ስነ አፈታት” ዘዴ ሊከተል የግድ ነውን? የሃይማኖት ምሁራንም ሆኑ በጠቅላላው ክርስቲያኖች እነዚህን ጉዳዮች ማወቅ ያለባቸው ለምንድን ነው? * መጽሐፍ ቅዱስ እንዴት እንደተፈጠረ በመለኮታዊና በሰዋዊ መለኪያዎች መካከል ያለውን ትክክለኛ ግንኙነት በትክክል ለማወቅ የሚያስችል የመጨረሻ መንገድ አለ? ይህን ነገር ሙሉ በሙሉ ማብራራት ባንችል ከልክ በላይ መጨነቅ ይኖርብናል? መልስህን አብራራ። * የመጽሐፍ ቅዱስን አመጣጥ ጥናታችንን በዘመናት ውስጥ ያሉ ክርስቲያኖች ሁልጊዜ ይዘውት በቆዩትና በሚያምኑት እውነት መጀመሩ በጣም አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?
1
የተማሪው ትግበራ እና አንድምታዎች
Made with FlippingBook - Online Brochure Maker