Bible Interpretation, Amharic Student Workbook

5 0 /

የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ-አፈታት

* ሁሉም የስነ አፈታት ዘዴዎች ጽሑፉ በተጻፈበት ዓለም እና በዘመናዊው ዓለም መካከል ያለውን ክፍተት ለማጥበብ የሚሞክሩበትን ምክንያት አብራራ? የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊዎችና እኛ የምንኖርበት ዘመን የተለያየ በመሆኑ ይህ በእርግጥ የሚቻል ነው ወይስ አስፈላጊ ነውን? * የእግዚአብሔርን ቃል ለመረዳት እና ተግባራዊ ለማድረግ ልቤን፣ አእምሮዬንና ፈቃዴን ለማዘጋጀት ምን እርምጃዎችን እወስዳለሁ? ከዚህ አንጻር ያለብኝስ ትልቁ ፈተና ምንድን ነው? * የመጽሐፍ ቅዱስ የመጀመሪያ ቅጂዎች በእግዚአብሔር መንፈስ አነሳሽነት የተጻፉና ‘ እስትንፋሰ እግዚአብሔር’ እንደሆኑ ለማመን ጽሑፎቹ ‘ስህተት አልባ’ እና ‘የማይታረሙ’ እንደነበሩ ማመን ያስፈልግሃል? መልስህን አብራራ። * በዚህ ትምህርት ላይ ካነበብካቸው ጽንሰ ሐሳቦች ሁሉ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስለተገለጸው መለኮታዊና ሰብዓዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ባሕርይ ይበልጥ አሳማኝ ሆኖ ያገኘኸው የትኛው ነው? የትኛውስ ነው የማያሳምንህ? ለምን? * የከተማ ክርስቲያን መሪዎች ከዘመናዊው የመጽሐፍ ቅዱስ ትችት ጋር የተያያዙትን አጠቃላይ ንድፈ ሐሳቦች ማወቅ የሚያስፈልጋቸው እስከ ምን ድረስ ነው? እነዚህ ዘርፎች የእግዚአብሔርን ቃል ለግል ደቀ መዝሙርነት እና አገልግሎት በትክክል የማዋል ችሎታችንን ያሳድጉናል ወይስ እንቅፋት ይሆናሉ? አብራራ። * ከዘመናዊው የመጽሐፍ ቅዱስ ትችት ዋና ዋና ንዑስ ክፍሎች መካከል የከተማ ክርስቲያን መሪዎች የእግዚአብሔርን ቃል ለሕይወት እና ለአገልግሎት እንዲረዱ እና እንዲተገበሩ የተሻለውን ሀብት ሊሰጣቸው ይችላል ብለህ ታምናለህ? ወግ እና/ወይም ቅዱሳት መጻሕፍት በዛሬው ጊዜ ለሚገኙ አብዛኞቹ ክርስቲያኖች የቤተ ክርስቲያን ሥልጣን ከግል የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጓሜው በላይ ቦታ አለው። የካቶሊክ ክርስቲያኖች መጽሐፍ ቅዱስን ለመተርጎም የሚጠቀሙበት መመሪያና ተነሳሽነት የሚገኘው በሊቀ ጳጳሱ ሥልጣን ላይ ነው፤ ምንም እንኳን መጽሐፍ ቅዱስ የግል አተገባበር ቢኖረውም እንደ ግል መጽሐፍ ብቻ መተርጎም የለበትም ይላሉ። ክርስቲያን መሆን፣ በክርስቶስ ውስጥ እውነትን አጥብቀው ከያዙት ሁሉ ጋር በዘመናት ሁሉ የዘላለም ሕይወት ተስፋን የሙጥኝ ያሉት የክርስቶስ ታማኝ የ “የቅዱሳን ኅብረት” አካል መሆን ነው ይላሉ። ብዙ ፕሮቴስታንቶች ግን መጽሐፍ ቅዱስን እንደ “የማይሻር” እና “የማይሳሳት” መጽሐፍ አድርገው ይመለከቱታል። የዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ አመለካከት ብቸኛው ችግር በሺዎች የሚቆጠሩ ራሳቸውን የቻሉ እንቅስቃሴዎችን እና ኑፋቄዎችን ማፍራቱ ነው፣ እነዚህ ሁሉ ከ”መጽሐፍ ቅዱስ ሥልጣን ጋር ግንኙነት አላቸው”። ስለ ትውፊቶች እና ቅዱሳት መጻሕፍት እንዲሁም በመጽሐፍ ቅዱስ ትርጓሜ ውስጥ ትውፊት ሊኖረው ስለሚገባው ሚና እነዚህን መከራከሪያዎች እንዴት ልንመለከታቸው ይገባል?

1

ጥናቶች

1

Made with FlippingBook - Online Brochure Maker