Bible Interpretation, Amharic Student Workbook

/ 6 1

የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ-አፈታት

የመንፈስ ቅዱስን አሳብ መለየት ዘዴዬ ነው መጽሐፍ ቅዱስን ለማጥናት ግልጽና ምክንያታዊ የሆነ ዘዴ ማዘጋጀት የቅዱሳት መጻህፍትን ትርጉም ለመረዳት በጣም አስፈላጊ እንደሆነ ብዙዎች ቢያምኑም ዛሬም ቢሆን ብዙዎች ደግሞ የመጽሐፍ ቅዱስን ትርጉም ለመረዳት የሚያስችል ዘዴ ማዘጋጀት አስፈላጊ መሆኑን ይጠራጠራሉ። መጽሐፍ ቅዱስን በተመለከተ በዘመናችን የሚቀርቡት ትችቶች ያስከተሉትን ጥርጣሬና ግራ መጋባት በመመልከት ብዙዎች ለአንድ የተወሰነ ዘዴ ታማኝ መሆን ለጥናት አደገኛ ነው የሚል አመለካከት አላቸው። እነዚህ ሳይንሳዊ የአቀራረብ ዘዴዎችን ከመጠቀም ይልቅ ለመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የበለጠ መንፈሳዊና ሊታወቅ የሚችል አቀራረብ ስለማግኘት ይከራከራሉ። የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናትን እንደ አእምሮአዊ ሳይሆን እንደ መንፈሳዊ ልምምድ ነው የሚመለከቱት፣ ስለዚህም በራሱ በመንፈስ ቅዱስ መማር ይፈልጋሉ። ይህ ደግሞ እንደ አንዳንድ ግትር ዘዴዎችን እንደመከተል ሳይሆን መንፈስ ቅዱስ ራሱ አስተማሪያቸው እንዲሆን የሚፈቅድ የልብ እና የነፍስ ዝግጅት ተደርጎ ይወሰዳል። ታዲያ የእግዚአብሔር ቃል እውነተኛ አስተማሪ መንፈስ ቅዱስ ብቻ ከሆነ ቅዱሳት መጻሕፍትን የማንበብ፣ የማጥናትና የመተግበር ዘዴን መፈለግ ያለው ጠቀሜታ ምንድነው? በመጽሐፍ ቅዱሳዊ አተረጓጎም ዘዴ ላይ የሚኖረን ጥረት የእግዚአብሔርን ቃል ያለንን ግንዛቤ ሊረዳን ወይም ሊያደናቅፍ የሚችለው በምን መልኩ ነው? አመለካከት እና ዘዴ፦ መጽሐፍ ቅዱስን ለመተርጎም በጣም አስፈላጊ የሆነው ዘዴ የትኛው ነው? ብዙዎች ቅዱሳት መጻሕፍትን በሥርዓት ማጥናታቸው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያለውን የእግዚአብሔርን ዓላማና ትርጉም ለመረዳት ጠቃሚ እንደሆነ ቢገነዘቡም በአመለካከትና በጥናት ዘዴ መካከል ያለውን ጠቀሜታ እንዴት መመዘን እንዳለብን ግልጽ አይደለም። በአንድ በኩል፣ ብዙዎች ትክክለኛ አስተሳሰብ ከሌለ የቅዱሳት መጻሕፍትን መረዳት እንደማይቻል ያምናሉ። የመጽሐፍ ቅዱስን ትርጉም ለማወቅ የምንጠቀምበት ዘዴ ምንም ይሁን ምን፣ እግዚአብሔር በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ በሙሉ እንደሚናገረው ትሑት፣ የተሰበረ፣ እና የተዋረደን መንፈስ ይጠይቃል። በሌላ በኩል ደግሞ፣ ከእውቀት የተነጠሉ ትሕትና እና ደግነት፣ ቅንዓት እና ጥልቅ ስሜቶች አላስፈላጊ መንፈሳዊ ቀውሶችን ያመጡበትን ብዙ ምሳሌዎችን መጥቀስ እንችላለን። ከእውቀት የተለየ አስተሳሰብ መንፈሳዊ ማስተዋልን ሳይሆን አምባገነንነትን፣ ግራ መጋባትን አልፎ ተርፎም መናፍቅነትን ያስከትላል። ትክክለኛ የልብ ዝግጅትና አመለካከት በመከተል እንዲሁም መጽሐፍ ቅዱስን በሚገባ በማጥናትና በመመርመር መካከል ያለው ዝምድና ምንድን ነው? በቅዱሳት መጻሕፍት ጥናታችን ውስጥ እንዴት በቅደም ተከተል ማስቀመጥ ይኖርብናል?

2

2

3

Made with FlippingBook - Online Brochure Maker