Bible Interpretation, Amharic Student Workbook
/ 7 9
የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ-አፈታት
• የሶስት ደረጃ ሞዴልን ለመጠቀም የመጀመሪያው እርምጃ የጽሑፉን ዝርዝር ሁኔታ፣ የመጽሐፉን አመጣጥ፣ ደራሲውን እና ተደራሲውን፣ የተፃፈበትን ዓላማ፣ እንዲሁም በተለያዩ ትርጉሞች የሚሰጠውን ትርጉም አተረጓጎም መመልከት ነው። • የጽሑፉን ወይም ምንባቡን አጠቃላይ መርሆች ማግኘት የሶስት-ደረጃ ሞዴል ሁለተኛ ደረጃ ነው፣ እና በጽሁፉ ውስጥ የተካተቱትን ማዕከላዊ መልዕክቶችን፣ እውነቶችን፣ ትዕዛዞችን ወይም ትምህርቶችን ማግኘትን ያካትታል። ይህ ደረጃ ጽሑፉ በዋናው ዓውድ ውስጥ ምን ማለት እንደሆነና አሁን በእኛ ሕይወት ውስጥ ወደሚኖረው ትርጉም መሄድን ያካትታል። እነዚህ መሠረታዊ ሥርዓቶች በመላው ቅዱሳን መጻሕፍት ውስጥ ካሉት ትምህርቶች ጋር ተነፃጽረው ለተጨማሪ ጥናትና ተግባራዊነት በግልጽ መቀመጥ አለባቸው። • ዝርዝሮቹን ከተመለከትን እና መርሆችን ካወጣን በኋላ፣ ወደ ሶስት ደረጃ ሞዴል ሦስተኛው ደረጃ እንሄዳለን፣ እርሱም በመንፈስ ቅዱስ ኃይል መንፈሳዊ መርሆችን በህይወታችን ውስጥ ተግባራዊ ማድረግ ነው። ተግባር መንፈስ እንደመራን ለእግዚአብሔር እውነት ልብን የማፍሰስ መገለጫ ነው። ለሕይወታችን የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለመታዘዝ ማስተዋልን እና ዝግጁነትን ይጠይቃል። • ሁሉም የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች የተሰጡት በክርስቶስ ደቀ መዝሙርነታችንን ለማጠናከር ሲሆን በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ አጽንዖት በተሰጣቸው የጋራ ጭብጦች ላይ ልዩነት ያሳያሉ። ለእግዚአብሔር እና ለባልንጀራችን ያለንን ፍቅር እንዲሁም ነፃነታችንን ሌሎችን ለማነጽና እግዚአብሔርን ለማክበር መጠቀማችን በብሉይም ሆነ በአዲስ ኪዳን የመጽሐፍ ቅዱስ የሥነ ምግባር መርሆዎች ዋና ዋና ክፍሎች ናቸው። ቅዱሳት መጻሕፍትን ለመተርጎም ቁልፉ ትሕትና መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል ስለሆነ በትሕትና ማንበብ፣ በማሰላሰልና በማጥናት በጸሎትና በጥሞና፣ ለመረዳትና ለመታዘዝ ስንሞክር የመንፈስ ቅዱስን እርዳታ መጠየቅ፣ ኃጢአታችንን መናዘዝ እንዲሁም ልብን፣ ዓላማንና ግንኙነታችንን ለማጽዳት ጥረት ማድረግ እጅግ አስፈላጊ ነው። በእነዚህ ጉዳዮች ላይ ስኬታማ አለመሆን እንዲሁ ምሁራንን ሊያፈራ ይችል ይሆናል እንጂ የበሰሉ ክርስቲያኖችን አያፈራም። ከሁሉም በላይ ደግሞ አንድ ቀን “ወደዚህ ትሁት፣ መንፈሱም ወደተሰበረ፣ በቃሌም ወደሚንቀጠቀጥ ሰው” ለሚለው ቃል መልስ መስጠት እንዳለብን ማስታወስ ይኖርብናል። (ኢሳ. 66.2).
2
~ Carson, Donald A. New Bible Commentary: 21st Century Edition. (electronic ed. of the 4th ed.). Downers Grove, IL: InterVarsity Press, 1997.
Made with FlippingBook - Online Brochure Maker