Bible Interpretation, Amharic Student Workbook

8 0 /

የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ-አፈታት

I. የ1 ቆሮንቶስ 9: 1-14 ጥናት:- ዝርዝሮቹን ተመልከት (በአባሪው ውስጥ ባለው “የትርጓሜ ቁልፎች” ውስጥ የሚገኘውን ተመሳሳይ ቅደም ተከተል ተከተል) 1ኛ ቆሮንቶስ 9: 1 - 14 - “እኔ ነጻ አይደለሁምን? ሐዋርያስ አይደለሁምን? ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስንስ አላየሁትምን? እናንተስ በጌታ ሥራዬ አይደላችሁምን? የሐዋርያነቴ ማኅተም በጌታ እናንተ ናችሁና ለሌሎች ሐዋርያ ባልሆን ለእናንተስ ምንም ቢሆን ሐዋርያ ነኝ። ለሚመረምሩኝ መልሴ ይህ ነው። ልንበላና ልንጠጣ መብት የለንምን? እንደ ሌሎቹ ሐዋርያትና እንደ ጌታ ወንድሞች እንደ ኬፋም፥ እኅት ሚስታችንን ይዘን ልንዞር መብት የለንምን? ወይስ ሥራን ለመተው መብት የሌለን እኔና በርናባስ ብቻ ነን? ከቶ በገዛ ገንዘቡ በወታደርነት የሚያገለግል ማን ነው? ወይስ ወይን ተክሎ ፍሬውን የማይበላ ማን ነው? ወይስ መንጋ እየጠበቀ ከመንጋው ወተት የማይጠጣ ማን ነው? ይህን በሰው ሥልጣን ብቻ እላለሁን? ሕግስ ደግሞ ያን አይልምን? የሚያበራየውን በሬ አፉን አትሰር ተብሎ በሙሴ ሕግ ተጽፎአልና። እግዚአብሔርስ ስለ በሬዎች ይገደዋልን? ይህን የሚለው ፈጽሞ ስለ እኛ አይደለምን? የሚያርስ በተስፋ ሊያርስ የሚያበራይም እንዲካፈል በተስፋ ሊያበራይ ስለሚገባው በእውነት ስለ እኛ ተጽፎአል። እኛ መንፈሳዊን ነገር የዘራንላችሁ ከሆንን የእናንተን የሥጋዊን ነገር እኛ ብናጭድ ትልቅ ነገር ነውን? ሌሎች በእናንተ ላይ ይህን መብት የሚካፈሉ ከሆኑ እኛማ ይልቁን እንዴታ? ነገር ግን የክርስቶስን ወንጌል እንዳንከለክል በሁሉ እንታገሣለን እንጂ በዚህ መብት አልተጠቀምንም። በመቅደስ ነገር የሚያገለግሉ ከመቅደስ የሆነውን ነገርን እንዲመገቡ፥ በመሠዊያውም የሚጸኑ ከመሠዊያው እንዲካፈሉ አታውቁምን? እንዲሁ ደግሞ ወንጌልን የሚሰብኩ ከወንጌል ቀለብ እንዲቀበሉ ጌታ ደንግጎአል።”

የቪዲዮ ሴግመንት 2 ዝርዝር

2

ሀ. እግዚአብሔር እውነትን እንድታውቅ እንዲረዳህ ጠይቀው።

1. የቅዱሳት መጻህፍት ባለቤት መንፈስ ቅዱስ ነው፣ 2 ጴጥ. 1.20-21.

2. የቅዱሳት መጻህፍት ደራሲ እንደመሆኑ መጠን ትርጉሙን ሊያስተምረን ይችላል። - 1 ዮሐንስ 2:20

3. መንፈስ ቅዱስ በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙትን ሐሳቦች እንድንረዳ ይረዳናል

ሀ. ዮሐንስ 15: 26-27

Made with FlippingBook - Online Brochure Maker