Bible Interpretation, Amharic Student Workbook

9 4 /

የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ-አፈታት

4. ምንም አይነት ተግባር ቢሆን፣ በግልፅ እና ለእግዚአብሔር ክብር ልናደርገው ይገባናል።

ሀ. ቆላ. 3.17

ለ. 1 ጴጥ. 4.11

ሐ. 1 ቆሮ. 10.31

ማጠቃለያ

2

» የሶስት-ደረጃ ሞዴል በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ ቁሳቁሶችን (ቃላትን፣ አንቀጾችን፣ ምዕራፎችን፣ መጻሕፍትንና ክፍሎችን) በመጠቀም ውጤታማ በሆነ መልኩ ጥቅም ላይ ሊያውል የሚችል የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጓሜ ውጤታማ ዘዴ ነው። » የእግዚአብሔርን ቃል በጥንቃቄና በጸሎት መመርመራችን በውስጡ የሚገኘውን ውድ እውነትና ግንዛቤ እንድናገኝ ይረዳናል።

ከዚህ ቀጥሎ የቀረቡት ጥያቄዎች በዚህ በሁለተኛው ሴግመንት የቀረቡትን ሀሳቦች መለስ ብለህ ለመቃኘት እንዲረዱህ ነው፡፡ ባለፈው ክፍል ላይ እንደነበረው ሁሉ በዚህ ክፍል ላይም የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጓሜ የሶስት ደረጃ ሞዴል የመጽሐፍ ቅዱስን ትርጉም ለመለየት እንዴት በጣም ውጤታማ ዘዴ ሊሆን እንደሚችል እንመለከታለን፤ እንዲሁም ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ሰዎች በጻፈው የመጀመሪያ ደብዳቤው 9.1-14 ላይ ያለውን ጽሑፍ በማጥናት እንዴት ጥቅም ላይ እንደሚውል እናያለን። ልክ እንደ ማንኛውም ክህሎት፣ የመጽሐፍ ቅዱስን የትርጓሜ ዘዴ በብዙ ጥረት፣ ረጅም ልምምድ እና ጠንቅቀው ከሚያውቁት በመማር ማዳበር ይቻላል። በዚህ ዘዴ ክህሎት ለማግኘት የመጀመሪያው እርምጃ ውጤታማ በሆነው የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ዘዴ ውስጥ የተካተቱትን የተለያዩ ደረጃዎች መረዳት ነው። ከዚህ በታች ባሉት ጥያቄዎች አማካኝነት እስካሁን የተረዳኸውን ነገር ገምግም፤ ከዚያም በቪዲዮ ሴግመንቱ ላይ ዘዴው በተግባር የተገለጸበት መንገድ ላይ አተኩር። 1. የሶስት ደረጃ ሞዴል በጠቅላላው ወይም በአንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል (ቃላት፣ አንቀጾች፣ ምዕራፎች፣ መጻሕፍት፣ ክፍሎች) ውስጥ ውጤታማ የመጽሐፍ ቅዱስ የትርጓሜ ዘዴ መሆኑን ማረጋገጥ የሚችለው እስከ ምን ድረስ ነው? ከላይ በምሳሌህ ላይ፣ በ1ኛ ቆሮንቶስ 9.1-14 እንደተገለጸው ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ሰዎች የሰጠው መመሪያ ምን አይነት ነው?

መሸጋገሪያ 2

የተማሪው ጥያቄዎችና ምላሾች

Made with FlippingBook - Online Brochure Maker