Bible Interpretation, Amharic Student Workbook
/ 9 5
የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ-አፈታት
2. የእግዚአብሔርን ቃል ስናጠና ሁልጊዜም ቢሆን እግዚአብሔር ጥበብ፣ ምሪትና መመሪያ እንዲሰጠን በመጸለይ መጀመር ያለብን ለምንድን ነው? ቃሉን ስናጠና እግዚአብሔር ብቻ ሊሰጠን የሚችለውን ጥበብ ለማግኘት እውነተኛ ልመናችን ባዶ ልማድ እንዳይሆን መጸለይ የምንችለው እንዴት ነው? 3. የመጽሐፍ ቅዱስን መልእክት ያለ መንፈስ ቅዱስ እርዳታ መረዳት የማይቻለው ለምንድን ነው? (1ቆሮ. 2.9-16)? እንዲሁም ደግሞ ለምንድነው ለመንፈስ ቅዱስ ምሪት መጸለይ በራሱ፣የእግዚአብሔርን ቃል ጠንከር ባለ እና ሥርዓት ባለው መልኩ ለሚደረግ ጥናት ምትክ የማይሆነው ለምንድነው? መልስህን አብራራ። 4. የ1 ቆሮንቶስ 9:1-14ን ስናጠና በሶስት ደረጃ ሞዴል ውስጥ እንደመጀመሪያ ደረጃ የተጠቀምነው ምንድነው? እነዚህ መሳሪያዎች የመጀመሪያውን ሁኔታ፣ ማለትም ጳውሎስ በራሳቸው አውድ ውስጥ ለቆሮንቶስ ሰዎች ሊነግራቸው ያሰበውን በተሻለ ሁኔታ እንድንረዳ የሚረዱን እንዴት ነው? 5. ጽሑፉ የተጻፈበትን የመጀመሪያ ሁኔታ ለማወቅ በምንፈልግበት ጊዜ ልንጠይቃቸው የሚገቡን ጥያቄዎች የትኞቹ ናቸው? ለእነዚህ ጥያቄዎች መልስ መስጠት የምንችለውስ እንዴት ነው? 6. “የቅዱሳት መጻህፍት አጠቃላይ መሠረታዊ መርህ” ለሚለው ትርጓሜ ስጥ። የእግዚአብሔርን ፈቃድ ይበልጥ በተሟላ ሁኔታ ለመረዳት ምሳሌዎች፣ አባባሎችና ሌሎች አጠቃላይ መሠረታዊ መርሆች የሚረዱን እንዴት ነው? 7. በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሦስት ማጠቃለያ መግለጫዎችን ወይም አጠቃላይ መርሆችን ምሳሌዎችን ስጥ። በግል ጥናትህ ላይ ያቀረብከው ማጠቃለያ የቅዱሳት መጻሕፍት መሠረታዊ መርህ መሆኑን እንዴት ማወቅ ትችላለህ? የአንተ ግኝት የቃሉ መርህ መሆኑን ወይም አለመሆኑን ለማረጋገጥ ምን ማድረግ አለብህ? 8. የመጽሐፍ ቅዱስን ትርጉም በሕይወታችን ውስጥ ተግባራዊ ለማድረግ የእግዚአብሔርን ሐሳብ መረዳት ያለብን ለምንድን ነው? በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ለሚገኘው ትምህርት ምላሽ ለመስጠት ለእግዚአብሔር ከልብ የመነጨ ታዛዥነታችንን በመግለጽ ረገድ ነፃነት ምን ሚና አለው? 9. የእግዚአብሔርን ቃል በሕይወታችን ውስጥ ተግባራዊ ለማድረግ በምንጥርበት ጊዜ ስለ ክርስቶስና ስለ መንግሥቱ የሚናገረውን ጠቅለል ያለ የቅዱሳት መጻሕፍትን መልእክት ማስተዋላችን አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? በእያንዳንዱ የቅዱሳት መጻህፍት ንባብና ትግበራችን ላይ ክርስቶስን ዋና ማዕከል ካላደረግን ምን ዓይነት ስህተቶች ሊፈጠሩ ይችላሉ? (ዮሐንስ 5:30-47)ን አንብብና ኢየሱስ ራሱ ፈሪሳውያን መጽሐፍ ቅዱስን በማንበብ በውስጡ ያለውን ትርጉምና መልእክት ለማስተላለፍ ክርስቶስን እንደ ማዕከል አድርገው ባለመመልከታቸው የሰጣቸውን ተግሣጽ ተነወያዩበት።)
2
Made with FlippingBook - Online Brochure Maker