Church PLANT Manual, Amharic Edition
116 • የቤተ ክርስቲያን ተከላ መምሪያ
• አፈጻጸሙን የሚከታተል ሰው ማን ነው?
ማስታወሻ፥ አንዳንድ ቡድኖች ኀላፊነት የሚሰጠውን ሰው በቀለማት፣ ወይም በተከላ ሂደት ለመለየት የሚጠቀሙ ሲሆን ሌሎች ከነአካቴው ምንም ቀለማት አይጠቀሙም።
3. እያንዳንዱን ማስታወሻችሁን ተገቢ በሆነው ወር ሥር አስፍሩ። 4. ቀደም ሲል ባወጣችሁት ዕቅድ ውስጥ ማስተካከያ ማድረግ የሚያስፈልገው ነገር ካለ ተመልከቱ። • ተግባራትን ለላ ጊዜ ማሻገር • ተግባራትን ወደ ፊት ወይም ወደ ኋላ ማድረግ • ዐዲስ ዐሳብ መጨመር • አንዳንድ ዐሳቦችን ማውጣት 5. ማስታወሻዎቹን በወረቀቱ ላይ አኑሯቸው። ወረቀቱን ጠቅልላችሁ ወደ ቤታችሁ ውሰዱትና በድጋሚ መሥራት ትችሉ እንደሆነ ተመልከቱ። • በሰነድ ቅጹ ላይ ያሉ ውጤቶችን ጠቅለል አድርጉ። 1. የራእያችሁን መግለጫና ሌሎች በቅጹ መጠይቅ ላይ ያሉ መረጃዎችን በሙሉ ጻፉ። 2. የተጠየቀው ሰነድ ርዝመት ከራእይ መግለጫችሁ የሚወሰድ ነው። ነገር ግን በአንዳንድ ጥቃቅን ጉዳዮች መደበኛ ሰነድ እንዲኖራችሁ ከፈለጋችሁ ዐጭር ልታደርጉት ትችላላችሁ። 3. ማስታወሻ፥ ወደ በኋላ ላይ የቡድን አባል ለመጨመር ከወሰናችሁ የምታካትቱን ሰው በመደበኛው የቡድናችሁ ሂደት ውስጥ ብታሳልፉት ይመከራል። ሌሎች ቡድኖች ደግሞ የቡድኑን ራእይና ግብ ሙሉ በሙሉ ሳይረዱና ቊርጠኛ ሳይሆኑ በሚጨመሩ አባላት ሊቸገሩ ይችላሉ።
Made with FlippingBook - Share PDF online