Church PLANT Manual, Amharic Edition
ክፍል 1፥ ዝግጅት • 17
ጥንቅቅ አድርጋ መሥራት አትችልም። በሁሉም የቤተ ክርስቲያን ተከላ ጥረቶች ውስጥ ግልጽነት ገዥ ነው። ዕሴቶቻችሁን ስትወስኑ ንጽጽሮችን ማስወገድ አለባችሁ። በአንድ ወቅት ቴዎዶር ሩዝቬልት “ማነጻጸር የደስታ ሌባ” ብለው የተናገሩት ነገር በበርካታ የሕይወት ገጽታዎች ውስጥ ሁሉ ተግባራዊ ሆኖ የሚታይ ሲሆን በተለይ ደግሞ በአገልግሎት ውስጥ በተለይም በቤተ ክርስቲያን ተከላ ዐውድ ውስጥ በጉልህ ይታያል። ቡድናችሁ፥ ለእያንዳንዱ የቡድኑ አባላት ጠቃሚ የሆኑ የተለያዩ ዕሴቶችን አሰባስቦ የጋራ የሆኑ ዕሴቶችን በመቅረጽ ኺደት በርካታ የዐሳብ ፍጭቶችን ማድረግ ያስፈልግ ይሆናል። በቡድናችሁ ውስጥ ያሉ አባላት ሁሉ ምልከታቸው የተቃኘበት የየራሳቸው ታሪክ ስላላቸው መጀመሪያ ላይ ይህን ማድረጉ አስቸጋሪ ሊመስል ይችላል። በዚህ ጉዞ ውስጥ ጥሩ ጥያቄዎችን መጠየቁ ጠቃሚ ይሆናል። በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ሁላችንም ወደ ቤተ ክርስቲያን ተከላ የምንመጣው በተመክሮዎቻችን ለመሆኑ አንዱ ማሳያ “ቀድሞ በነበርሁበት ቤተ ክርስቲያን ይህን ወይም ያን አድርገናል” ወይም “ነገሮችን የምናደርገው በዚህ ወይም በዚያ መንገድ ነው” የሚሉና የመሳሰሉት መግለጫዎቻችን ናቸው። የቤተ ክርስቲያን ተከላ ቡድናችሁ በሁሉም አቅጣጫ የጋራ ዕሴቶችን በመያዝ ንጽጽሮችን ማስወገድ ያስፈልጋል።
Made with FlippingBook - Share PDF online