Church PLANT Manual, Amharic Edition
18 • የቤተ ክርስቲያን ተከላ መምሪያ
ትምህርት 2 ቡድን ማዋቀር 1 ሬቨረንድ ሉክ ራፍሊ
ብዙውን ጊዜ ስኬት በቡድን መሥራትንም ያካትታል። “ድር ቢያብር አንበሳ ያስር” የሚለው አባባል ጠንካራ የሆነ የቡድን ሥራን ጠቃሚነት አጉልቶ የሚያሳይ ነው። በቡድን ስለመሥራት ጠቀሜታና አስፈላጊነት ብዙ ተጽፏል። እያንዳንዳችን በተለያዩ ዐውዶች ውስጥ ያሉ የተለያዩ ቡድኖችን መጠቆም እንችላለን (ለምሳሌ፥ ስፖርት፣ ንግድ፣ ውትድርና፣ ጥናትና ምርምር፣ ትምህርት፣ ወዘተርፈ)። ከእነዚህ ቡድኖች ውስጥ አንዳንዶቹ በብቃት ዪሠሩና ጥሩ ውጤቶችን የሚፈጥሩ ሲሆኑ ሌሎች ደግሞ በትግልና ምንም ማስተካከያ ባለማድረግ አባሎቻቸውን ለተስፋ መቍረጥና ለብስጭት ይዳርጋሉ። ይህ እውነታ ለቤተ ክርስቲያን ተከላ ቡድኖችም ቢሆን ተመሳሳይ ነው። በተመክሮዎች ብቻ ሳይሆን በቡድን እንድንሠራ የታቀድንና ለዚህ የተፈጠርን መሆናችንን የሚጠቁሙ በርካታ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መርሖች አሉ። እስቲ ለውጤታማ የቤተ ክርስቲያን ተከላ ቡድኖች መርሖችን የሚሰጡ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን እንመልከት። I. ግልጽነት እንደ ዋሽንትና እንደ በገና ያሉ ሕይወት የሌላቸው ነገሮች እንኳ የድምፃቸው ቃና ልዩነት ከሌለው ዜማቸውን እንዴት ማወቅ ይቻላል? ደግሞም መለከት ትክክል ያልሆነ የጥሪ ድምፅ ካሰማ፣ ለጦርነት ማን ይዘጋጃል? (1ቆሮንቶስ 14፥7-8) የጋራ ግልጽ ጥሪ አስፈላጊ መሆኑን ለመግለጽ ጳውሎስ የሙዚቃ መሣሪያዎችን በምሳሌነት ይጠቀማል። አነስተኛ የሙዚቃ ባንድም ይሁን ትልቁ ኦርኬስትራ ግልጽ የሆኑና የተስማሙባቸውን ሙዚቃዎች ይጫወታሉ። ያ ካልሆነ አስከፊ ውጤት መከተሉ አይቀርም። ቆንጆ ሙዚቃ ወዲያውኑ ማንንም ወደ የማያስደስት ጫጫታ ሊለወጥ ይችላል። ግልጽ ትእዛዝ ከሌለ ጠንካራ ወታደራዊ ኀይል ግራ ሊጋባ፣ ሊያፈገፍግ ብሎም ሊሸነፍ ይችላል። ውጤታማ ቡድኖች ስለሚሠሩት፣
1 በተጨማሪ ስኬታማ ቡድንን ስለመገንባት ለማንበብ Ripe for Harvest, pp. 169-180 ይመልከቱ።
Made with FlippingBook - Share PDF online