Church PLANT Manual, Amharic Edition

20 • የቤተ ክርስቲያን ተከላ መምሪያ

የተለዩ የሆኑትን ስጦታዎች ዋጋ መስጠትና ልዩነቶቹን አቀናጅቶ ሁሉም ሰው በጋራ ዐላማ ቤተ ክርስቲያንን ለማነጽ እንዲሠራ ማድረግ አስፈላጊ ነው። የቡድን መሪዎች የቡድናቸውን ጠባይ ለማወቅ የጸጋ ስጦታዎችን መለየት የሚያስችሉ ዘዴዎችንና እንዲሁም ተፈጥሯዊ ባሕርዮቻቸውን ለመለየት የሚያስችሉ መመዘኛዎች ተግባራዊ ማድረግ ይችላሉ። IV.መተግበርና ማስተካከያዎች ነህምያ የኢየሩሳሌምን ቅጥሮች መልሶ ለመገንባት በጣም ጠንካራ የሆነ ዕቅድ ዐወጣ (ነህምያ 4፥15-23)። ሥራው በጣም ታላቅ ቢሆንም ቡድኑ በከፍተኛ ተነሣሽነትና በትጋት ሥራውን ይሠራ ነበር። ነህምያ፥ ቡድኑና እስራኤላውያን ሥራቸው በሚሠሩ ጊዜ ተቃውሞም ገጥሟቸው ነበረ። የነህምያ ቡድን ለገጠማቸው የጥቃት ስጋት መፍትሒ ለማበጀት አቀራረባቸውን ማስተካከል ነበረባቸው። ነህምያ፥ የግንባታ ቡድኑን ደኅናነታቸው ተጠብቆ እንዲሠሩና አስፈላጊም ከኾነ ተገቢውን ምላሽ እንዲሰጡ እንደገና አዋቅሮ አስተባበራቸው። ካደረገው ማስተካከያ የተነሣ በርካታ ሥራ መሠራት ቻለ ይሁን እንጂ ተግዳሮቶችም ነበሩ። ውጤታማ ቡድኖች ዕቅድ አላቸው፤ዕቅዱን ከልባቸው ይተገብራሉ፤ እንዲሁም የሚገጥሟቸውን ዐዳዲስ ችግሮች ለመጋፈጥ ዕቅዶቻቸው ላይ ማስተካከያዎች ያደርጋሉ። V. ተግባቦትና ቅንጅት ከላይ በተጠቀሱት በእያንዳንዱ የቅዱሳት መጻሕፍት መካከል ግንኙነትና ተዛማጅነት አለ። ግልጽ ስሜት ሊኖረን ይችላል ነገር ግን ይህ ሊሆን የሚችለው ራእዩ በቀላሉ ሌሎች የሚገባቸው ሲሆን ነው። የባለቤትነት ስሜት ሊኖርም የሚችለው በቃል ወይም በተግባር መቀራረብንና አንድነትን የሚፈጥር ተግባቦት ሲኖር ነው። ልክ እንዲሁ በአካል ክፍሎች ምሳሌ እንደተገለጸው ስጦታዎች የተሰጡት ተቀናጅተው አካሉን ለማነጽ ነው። ይህም የሚሆነው ጥሩ የተግባቦት መሥመር ሲኖር ነው። ነህምያ ተግዳሮቶች በገጠሙት ጊዜ አስተካክሎ ሥራው መቀጠል የቻለው በተደራጀ ቅንጅትና ጠንካራ ተግባቦት ነው።

Made with FlippingBook - Share PDF online