Church PLANT Manual, Amharic Edition

ክፍል 1፥ ዝግጅት • 21

VI.ባለ ሥልጣንና ሐዋርያዊ በአንጾኪያ ባለችው ቤተ ክርስቲያን ነቢያትና መምህራን ነበሩ፤ እነርሱም፦ በርናባስ፣ ኔጌር የተባለው ስምዖን፣ የቀሬናው ሉክዮስ፣ የአራተኛው ክፍል ገዥ የሄሮድስ ዐብሮ አደግ የነበረው ምናሔና ሳውል ነበሩ። እነዚህም ጌታን እያመለኩና እየጾሙ ሳሉ፣ መንፈስ ቅዱስ፣ “በርናባስንና ሳውልን እኔ ለጠራኋቸው ሥራ ለዩልኝ” አለ። እነርሱም ከጾሙና ከጸለዩ በኋላ እጃቸውን ጭነው አሰናበቷቸው (ሐዋርያት ሥራ 13፥1-3)። እነዚህ ባሕርያት ለቤተ ክርስቲያን ተከላ ቡድኖች ልዩ የኾኑ ባሕርያት ናቸው። የተለያዩ ቡድኖች የተለያዩ ዐላማዎችና ግቦች ላይ የሚያተኩሩ ሲኾን የቤተ ክርስቲያን ተከላ ቡድን ግን ትኩረቱ ክርስቶስን ያማከለ ደቀ መዛሙርትን የማፍራት ሥራ ነው። በዚህ ሥራ ውስጥ የሚካፈለው ማንኛውም ሰው ሳይሆን በቤተ ክርስቲያን ሥልጣን የተሰጣቸውና የኢየሱስን ትእዛዛት ሌሎች እንዲታዘዙ ለማስተማር የተላኩ ናቸው። ስኬታማ የቤተ ክርስቲያን ተከላ ቡድኖች ወደ ሥራቸው የሚሰማሩት በመንፈስ ቅዱስ ምሪት ነው። VII. ምዘና ጳውሎስ ከጥቂት ጊዜ በኋላ በርናባስን፣ “ተነሣና የጌታን ቃል ወደ ሰበክንባቸው ከተሞች ሁሉ እንሂድ፤ በዚያ ያሉ ወንድሞችም በምን ሁኔታ እንዳሉ ለማወቅ እንጐብኛቸው” አለው (ሐዋርያት ሥራ 15፥36)። ጳውሎስ የምዘናና የግምገማን አስፈላጊነት በግልጽ አሳይቷል። እያንዳንዱ ስኬታማ ቡድን ሊሠሩ ያሰቡትን ነገር ማሳካታቸውን ይገመግማሉ። ይህን ሲያደርጉም በቀጣይ ስኬታቸውን ዘላቂ ለማድረግ ይወስናሉ። ግባቸውጋ ለመድረስ ሊከተሏቸው የሚገቡ ርምጃዎችን ይወስናሉ። ልክ እንዲሁ የእናንተም ቡድን እንደ ቡድን ምን ያህል እየሠራችሁ እንደሆነ መገምገምና በቀጣይ እንዴት ውጤታማ ልትሆኑ እንደምትችሉ መመዘን ያስፈልጋችኋል። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እግዚአብሔር ሰዎችን ያገናኘባቸው ልዩ ልዩ መንገዶች እንዳሉ ምሳሌዎችን መመልከት እንችላለን። ሙሴን ከአሮን፣

Made with FlippingBook - Share PDF online