Church PLANT Manual, Amharic Edition
4 • የቤተ ክርስቲያን ተከላ መምሪያ
ይሰጣሉ። እስከዚያው ድረስ ሰዎች ወይ በቤተ ክርስታያን ውስጥ ወይም በዓለም ኾነው ይኖራሉ። ዓለም በሰይጣን ተጽዕኖ (ቍጥጥር) ሥር ነው።በአንጻሩ ደግሞ ቤተ ክርስቲያን በመንፈስ ቅዱስ ተጽዕኖ (ቍጥጥር) ሥር ነች። የቤተ ክርስቲያን ተከላንና አስፈላጊነትን ለመረዳት ይህ ቍልፍ ነው። በኤፌሶን 2፥12-22 እና ኤፌሶን 3፥10-21 ያሉትን ሁለት ክፍላተ ምንባብ ማሰቡ ጠቃሚ ነው። እነዚህ ምንባባት “ለምን ተጨማሪ አብያተ ክርስቲያናት ያስፈልጉናል?” ለሚለው ጥያቄ ሁለት መልሶችን ይሰጡናል። የመጀመሪያው እና በጣም ግለጽ የሆነው እግዚአብሔር የሚሠራው በቤተ ክርስቲያን ውስጥ (በሕዝቡ መካከል) ነው። በሌላ አነጋገር ይህ ማለት ቤተ ክርስቲያን የእግዚአብሔር ድነት፣ የመንፈስ ቅዱስ የሚያበረታ ሀልዎት፣ እና የመንግሥቱ ሕይወት ትክክለኛ መገለጫና ምስክር “መገኛ” (ቦታ፣ ዐውድ) ናት ማለት ነው። የርሱ ፍላጐት በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ዐዲሱን ሰው መፍጠር ነው። ሁለተኛው፥ እነዚህ ምንባባት እግዚአብሔር በቤተ ክርስቲያን በኩል (በሕዝቡ በኩል) አንደሚሠራ ያሳያሉ። ይህን እውነት በሌላ መንገድ ለመግለጽ፣ ቤተ ክርስቲያን የመንግሥቱን ዐላማ በዓለም ላይ ለማስፋት ዝግጁና ፈቃደኛ የኾነች የእግዚአብሔር “ወኪል” ነች ማለት ይቻላል። በቤተ ክርስቲያን በኩል እግዚአብሔር ዓለምን ከራሱ ጋራ ያስታርቃል። 2 መጽሐፍ ቅዱሳዊው እውነት፥ በጠላት ጥቃት፣ ባርነት፣ ክፍፍል፣ እና መቅበዝዝ ሥር ለወደቁ ሁሉ ብቸኛ ተስፋ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ናት። ምንም እንኳ የርሱ አስሚታ በሁሉ ቦታ ቢሆንም ቤተ ክርስቲያን ግን የእግዚአብሔር መገኛ እና ወኪል በመኾን በዚህ ጨለማ ዓለም ውስጥ ሰዎች ነጻነትን የሚጐናጸፉበትን ዕድል ታመቻቻለች። እግዚአብሔር ይመስገን “የዲያብሎስን ሥራ ሊያፈርስ” ኢየሱስ መጣ (1 ዮሐንስ 3፥8)።
2 ቤተ ክርስቲያን “መገኛ ስፍራ” እና “ወኪል” መኾኗን ለመረዳት “Theology of the Church for Team Leaders” in The Timothy Conference Workbook , Wichita: TUMI Press, 2005, pp. 39-46. ይመልከቱ
Made with FlippingBook - Share PDF online