Church PLANT Manual, Amharic Edition

ክፍል 2፥ መጀመርና መሰባሰብ • 43

ኢየሱስ ነው። እኛ ያልተሳካልንን ነገር ሁሉ ርሱ አሳክቷል። ርሱን እንድናመልከውና በርሱም ደስ እንድንሠኝ የፈጠረን፤ እኛ ግን በዐመፃችን ያሳዘንነው ርሱ ታሪኩን ለማዳን ጣልቃ ገባ። II. የወንጌሉ ተልእኮ • ወንጌል፥ የሚያድነንና የክርስቶስን ተልእኮ እንድንፈጽም የሚልከን ምሥራች ነው። ኢየሱስ ተልእኮውን እንዲህ በሚል ዐጭር ቃል ገልጾታል “የሰው ልጅ የመጣው የጠፋውን ሊፈልግና ሊያድን ነው” (ሉቃስ 19፥10)። • ወንጌል ሲታወጅ ሰዎች ሰምተው እንዲረዱት ወንጌሉ ዐውዳዊ መሆን አለበት። ዐውዳዊ የማድረግ ሂደት ሲነሣ ብዙዎች ሐዋርያ ጳውሎስን ያስባሉ። ጳውሎስ እንዲህ አለ “ደካሞችን እመልስ ዘንድ፣ ከደካሞች ጋራ እንደ ደካማ ሆንሁ። በሚቻለኝ ሁሉ አንዳንዶችን አድን ዘንድ፣ ከሁሉም ጋር ሁሉን ነገር ሆንሁ። ይህን ሁሉ የማደርገው፣ ከወንጌል በረከት እካፈል ዘንድ፣ ስለ ወንጌል ብዬ ነው” (1ቆሮንቶስ 9፥19-23)። እንዲሁም “እኔ የክርስቶስን ምሳሌ እንደምከተል እናንተም የእኔን ተከተሉ” (1 ቆሮንቶስ 11፥1) ያለው ጳውሎስ ነው። በሌላ አገላለጽ ዐውዳዊነትን በተመለከተ የጳውሎስ ፍጹም ምሳሌ ኢየሱስ ነበረ። ዮሐንስም እንዲህ ብሎ ጽፏል “ቃልም ሥጋ ሆነ፤ በመካከላችንም ዐደረ፤ እኛም ጸጋንና እውነትን ተሞልቶ ከአባቱ ዘንድ የመጣውን የአንድያ ልጅን ክብር አየን” (ዮሐንስ 1፥14)። በክርስቶስ ትሥጕት የእግዘአብሔር መንግሥት ወደ ዓለም መግባቷን አየን። በክርስቶስ የዓለም ብርሃን ወደ ጨለማችን ዘልቆ ሲቤዥና ነጻ ሲያወጣ አየን። በእኛ በኀጢአተኞች ሰዎችና በቅዱሱ በእግዚአብሔር መካከል የነበረውን ግድግዳ አፍርሶ ኢየሱስ ቀረበን። • ኢየሱስም “አብ እኔን እንደ ላከኝ፣ እኔም እናንተን እልካችኋለሁ” አላቸው (ዮሐንስ 20፥21)።

Made with FlippingBook - Share PDF online