Church PLANT Manual, Amharic Edition

44 • የቤተ ክርስቲያን ተከላ መምሪያ

ወደ ከተሞቻችንና ባልንጀሮቻችን የወንጌሉን መልእክት እንድናደርስ ኢየሱስ እየላከን ነው። ነገር ግን የክርስቶስን ተልእኮ በብቃት እንፈጽም ዘንድ የተለያዩ የባህል ዐውዶችን ጠንቅቀን በመረዳት ብልኆች መሆን አለብን። ዐውዳዊነት የሚጠይቀው የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጓሜዎችን 2 ጠንቅቆ መረዳት ብቻ ሳይሆን በወንጌል የምንደርሳቸውንም ሰዎች ባህል ጠንቅቆ መረዳትን ይጠይቃል። ይህ የአተረጓጐም ሂደት ባህላችንን በወንጌል ተልእኮ መነጽር እንድንመለከት ይረዳናል። III.የወንጌሉ መንገድ • ወንጌሉ እኛን በማዳንና ለተልእኮ በማሠማራት ብቻ አላበቃም ነገር ግን ያበጀናልም። ኢየሱስ ወደ ወንጌሉ (ኢየሱስን መውደድ)፣ ወደ ባህሉ (ባልንጀሮቻችንን መውደድ)፣ እና ወደ ቤተ ክርስቲያን (ወንድሞችና እኅቶቻችንን መውደድ) ጠራን። በዳንን ወቅትና ለተልእኮ ከመሰማራታችን በፊት በአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ዐውድ ውስጥ በወንጌል ቅርጽ እንይዛለን። ቤተ ክርስቲያን፥ ዓለምን ለመድረስ የእግዚአብሔር ቀዳሚ ዕቅድ ናት። ኢየሱስ እንዲህ አለ፥ “በዚህ ዐለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፤ የገሃነም ደጆችም አያሸንፏትም” (ማቴዎስ 16፥18)። • ወንጌልና ተልእኮ እንዲሁ ከምንም ተነሥተው የሚመጡ ነገሮች አይደሉም። የቤተ ክርስቲያን ትኩረትና ዐላማዎች ናቸው፤ ወደ ክርስቶስና ወደ ቤተ ክርስቲያኑ የተጨመሩትን የእግዚአብሔርን ሕዝብ የሚያያይዙ አቀጣጣዮች ናቸው። ቤተ ክርስቲያን የእግዚአብሔርን አገዛዝ ምንነት ስለምትገልጽ የክርስትና ተልእኮ ወሳኝ ክፍል ናት። ተልእኮ፥ ለእግዚአብሔር ያለንን ፍቅር፣ለባልንጀሮቻችን ያለንን ፍቅር፣ እንዲሁም ርስ በርሳችን ያልነን ፍቅር ለሌሎች የምናሳይበት መድረክ ነው። 2 ሥነ ፍታቴ፥ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍላተ ምንባብ ትርጓሜ ለመረዳት እና ለመተርጎም እንዲሁም ቍልፍ መርሖችን ለማስቀመጥ የሚረዳ የጥናት መሣሪያ ነው። በሥነ ፍታቴ ሂደቶች ዙሪያ ተጨማሪ መረጃዎች ለማግኘት Rev. Dr. Don L. Davis, Bible Interpretation . The Capstone Curriculum, Module 5. (Wichita: TUMI Press, 2005) ይመልከቱ።

Made with FlippingBook - Share PDF online