Church PLANT Manual, Amharic Edition
ክፍል 2፥ መጀመርና መሰባሰብ • 45
ስለዚህ፣ ቤተ ክርስቲያን የምንናገረው ነገር ከምንኖረው ሕይወት ጋራ የሚገናኝ መሆኑን በሚገባ ማጤን አለባት። በዚህ አግባብ፥ የማይታየው አምላክ በእግዚአብሔር ሕዝቦች መዋደድ በኩል ይታያል (1ዮሐንስ 4፥12)። • ቤተ ክርስቲያን ከመሰባበሰቢያ ቦታ ያለፈች ናት። ቤተ ክርስቲያን በሰዎች መካከል የእግዚአብሔር መንግሥት መገለጫ ማሳያ ናት። በሌላ አገር የአንድ ሉዓላዊ አገርን ፍላጎት እንደሚወክል ኤምባሲ ቤተ ክርስቲያንም በዚህ ዓለም የእግዚአብሔር ኤምባሲ ናት። ቤተ ክርስቲያን በዚህ ዓለም ውስጥ የወንጌሉን ኅይልና ተጽዕኖ በሕይወታቸው የሚገልጡ እንደራሴዎች ናቸው። “ቤተ ክርስቲያን የእግዚአብሔር መንግሥት ማኅበረ ሰብ እንጂ በራሷ ንግሥት አይደለችም። መንግሥቱ የእግዚአብሔር የንግሥና የርሱ አገዛዝ በረከቶች የሚዳረስባቸው ቦታዎች ኹሉ ናቸው። በዚህ ረገድ ቤተ ክርስቲያን በእግዚአብሔርን አገዛዝ እና ንግሥና በረከቶች ሥር የተሰባሰቡ ሰዎች ማኅበር ናት። የእግዚአብሔር መንግሥት ቤተ ክርስቲያንን ፈጠረ፤ በቤተ ክርስቲያን በኩል ይሠራል፤ በቤተ ክርስቲያን በኩልም ለዓለም ይታወጃል።” 3 IV. መደምደሚያ የወንጌል መሪ ኀይል በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ተገልጿል፤ ኢየሱስ እንዲህ አለ “እነዚሁ መጻሕፍት ስለ እኔ የሚመሰክሩ ናቸው” (ዮሐንስ 5፥39)። ከዘፍጥረት እስከ ራእይ ያሉት መጻሕፍት ሁሉ ወደ አዳኛችንና ንጉሣችን ኢየሱስ የሚያመለክቱ ናቸው። ስለዚህ፥ ስትሰብኩ፣ ስታስተምሩ፣ እና ደቀ መዛሙርት ስታደርጉ እንዲህ የሚለው የጳውሎስ ንግግር ዘወትር በልባችሁ ይሁን “በመካከላችሁ ሳለሁ ኢየሱስ ክርስቶስን፣ ያውም የተሰቀለውን፣ እርሱን ብቻ እንጂ ሌላ እንዳላውቅ ወስኜ ነበርና” (1ቆሮንቶስ 2፥2)። የወንጌል መሪ ኀይል የጠፋውን ለማዳን የመጣውን የኢየሱስን ምሳሌ በምንከተልበት በተልእኮ ዐውድ ውስጥ ተገልጿል። ወንጌል ያድነናል
3
Mere Missions , p. 148.
Made with FlippingBook - Share PDF online