Church PLANT Manual, Amharic Edition

ክፍል 2፥ መጀመርና መሰባሰብ • 47

ትምህርት 5 ባህልንና ዐውድን ማሰስ 1 መጋቢ ሎሬንዞ ኤሊዞንዶ

የምንኖረው በፈጣን ለውጥ ውስጥ በሚገኝ ዓለም ውስጥ ነው። ከጥቂት ዓመታት ወዲህ በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ከተሞች የሕዝቦች መልከዓ ምድራወ አቀማመጥ በእጅጉ ተለውጧል። አብዛኛው የዓለማችን ሕዝብ በትላልቅ ዓለም አቀፍ ከተሞች ውስጥ መኖርን ምርጫው እያደረገ ይገኛል፤ ይህም እጅግ የበለጸጉ ከተሞችን ፈጥሯል። ይህ ለውጥና የሕዝብ እድገት በርካታ ማኅበረ ሰቦችን ከማስገኘቱም በላይ የተለያዩ የባህል ልዩነቶችንም ፈጥሯል። “ብዝኅነት” የሚለው ቃል ለዘመናችን ዐውድ እንግዳ ቃል ባይሆንም እንዲሁም የባህልን ልዩነት መረዳት አስፈላጊ እንደሆነ ብዙዎች ቢስማሙም ባህል ምን እንደሆነ ሊያብራሩ የሚችሉ ግን ጥቂቶች ናቸው። ቤተ ክርስቲያን ውጤታማ በሆነ መንገድ ወንጌሉን ለሰዎች እንድታደርስ እግዚአብሔር ስለጠራት ባህሎችን በማሰስና በመረዳት ረገድ የሠለጠንን ልንሆን ይገባል። I. ባህል ምንድን ነው? • ዶ/ር ዴቪስ ባህልን እንዲህ በማለት ይተረጉሙታል፦ “ባህል፥ የተቀናጀ፣ በደንብ የተመሠረተ፣ ማኅበረ ሰባዊ ብያኔ ብያኔ ያላቸውን ባሕርያትና በአስተሳሰብ፣ የራሱ የሆነ የግምገማ ሥርዐት ያለው ንጽረተ ዓለም ነው።” በቀላል አነጋገር ባህል የምንማረው ሥርዓትና የሥነ ምግባር ሲሆኑ እነዚህም ዕሴታቻችንና ንጽረተ ዓለማችንን የሚቀርጹ፣፣ በማኅበረ ሰቡ ውስጥ የሚኖረንን ማኅበራዊ መስተጋብር የሚቀርጽ ሥርዐት ነው። • እነዚህ የምንማራቸው ሥርዐቶችና ባሕርያት ከየት ነው የሚመጡት? እንዴትስ ነው የሚያድጉት? ይህን በተመለከተ ዶ/ር ዴቪስ ሦስት የባህል አቅጣጫዎችን ያብራራሉ።.

1 This seminar is rooted in the concepts of the seminar “The Difference That Difference Makes” in Ripe for Harvest , pp. 139-153.

Made with FlippingBook - Share PDF online