Church PLANT Manual, Amharic Edition
ክፍል 2፥ መጀመርና መሰባሰብ • 49
የሚበይኑ የሚያሳድጉና የሚመሩት ልዩ የሆኑት ክርስትያናዊ ባህሎች በእነዚህ ሦስት ቃላት ላይ የተመሠረቱ ናቸው። • ከሁሉ አስቀድሞ ክርስቲያናዊ ባህል በተፈጥሮው ልዕለ ተፈጥሯዊ ስለሆነ ፈጽሞ ከዓለም የተለየ ነው። • ሁለተኛው፦ ኢየሱስ ጌታ ነው የሚለው እውነት የቤተ ክርስቲያንን ምንነት ብቻ ሳይሆን እድገትም የሚገልጽ ነው። ቤተ ክርስቲያን በራሷ ስላልተፈጠረች እና ለራሷም ስለማትኖር ልዩ የሆነ ክርስቲያናዊ ባህል አላት። • በመጨረሻም፦ ኢየሱስ ጌታ ነው የሚለው እውነታ ቤተ ክርስቲያንን የሚመራትም ነው። ቤተ ክርስቲያን፥ የተዋጁ የእግዚአብሔር ሕዝቦች የትኛውንም ፖለቲካዊ፣ ብሔራዊ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ፣ ጾታዊ የባህል ገደቦችን ሁሉ የሚያልፍ ነው። ይህ የሆነው ግን በራሱ የተሻለ ወይም የላቀ ስለሆነ ሳይሆን ለመጽሐፍ ቅዱስ ሥልጣንና በቂነት በልዩነት ስለሚገዛ ነው። IV. መደምደሚያ የባህል አሰሳ ግቡ እያንዳንዱ ዐውድ የራሱ የሆነ ባህል እንዳለውና ውጤታማ ስብከተ ወንጌል ማድረግ የባህል ልዩነቶችን እንዳሉ መረዳት ነው። ይህም ዋነኛው ግባችን የሆነውን ሰዎችን ወደ ተመሳሳይ ባህል ሳይሆን ወደ ክርስቶስ የማምጣት ተልእኮ እንድንፈጽም የሚያስችለን ነው። ዐላማችን ሰዎች ያላቸውን የተለየ ባህል እንዲያጡ ማድረግ ሳይሆን ለኢየሱስ ጌትነት እንዲገዙ መምራት ነው። ልክ ኢየሱስ የባህል ግድግዳዎችን ጥሶ ወደ እኛ እንደመጣ እንዲሁ እኛም በዘመናችን ዐውድ ውስጥ የሚገኙ የባህል ዕንቅፋቶችን በማለፍ ወንጌልን ማወጅና መግለጥ አለብን። የቅዱሳት መጻሕፍትን ሥልጣትና ክርስቶስን መምሰልን ቅድሚያ በመስጠት አማኞች የባህል ልዩነቶችን በማለፍ ወንጌል ውጤታማ በሆነ መልኩ ማወጅና መግለጥ ይችላሉ።
Made with FlippingBook - Share PDF online