Church PLANT Manual, Amharic Edition

50 • የቤተ ክርስቲያን ተከላ መምሪያ

ትምህርት 6 ስብከተ ወንጌል እና ክትትል 1

ከዚህ ቀደም በነበሩት ትምህርቶች እንደተመለከትነው በቤተ ክርስቲያን ተከላ ዝግጅት ወቅት ቤተ ክርስቲያን የመትከል ራእይን ለማሳደግ የሚረዳ ታማኝ የክርስቲያኖች ቡድን ማዘጋጀት እንደሚያስፈልግ ተመልክተናል። ወደ ቤተ ክርስቲያን ተከላ የጅማሬና የመሰባሰብ ምዕራፍ ስንሻገር ከሌሎች አብያተ ክርስቲያናትና የምታውቋቸውን አማኞች በመመልመል ቤተ ክርስቲያናችሁን እንዲቀላቀሉ ለማድረግ የሚገፋፋውን ፈተናን ማስወገድ ይገባል። ጤናማ ቤተ ክርስቲያንን የሚፈልጉና በዚያም ማገልገል የሚሹ ክርስቲያኖችን መቀበል ምንም ስሕተት የለውም ይሁን እንጂ ይህ ተግባር ከእውነተኛ ቤተ ክርስቲያን እድገት ጋራ ሊምታታባችሁ አይገባም። ቤተ ክርስቲያን ያለችው የጠፉ (የማያምኑ) ሰዎች በጌታ ኢየሱስ እንዲያምኑ ለመርዳት ነው። ስለዚህ ስብከተ ወንጌልና የዐዳዲስ አማኞች በእግዚአብሔር ቤተ ሰብ ውስጥ መካተት የዕድገትና የውጤታማነት መለኪያ መሆን ይኖርበታል። ብዙ ክርስቲያኖች ከስብከተ ወንጌል ጋራ በተያያዘ ከሚሰማቸው ከፍተኛ ፍርሃት ጋራ ስለሚታገሉ የቤተ ክርስቲያን ተከላ ቡድናችሁንና የቤተ ክርስቲያን አባላትን የስብከተ ወንጌል ባሕርይን እንዲገነዘቡ፣ እምነታቸውን እንዴት ማካፈል እንደሚችሉ እንዲያውቁ መርካት በቤተ ክርስታያን ተከላው ሂደት ውስጥ ትልቅ ስፍራ የሚሰጠው ነገር ነው። ለስብከተ ወንጌል እያንዳንዱ ዐውድ የራሱ የሆነ ተግዳሮት አለው። ቀጥሎ የቀረበው ቢጋር ከስብከተ ወንጌል ጋራ የሚያያዙ ፍርሃቶችን ለማስወገድ እና ዐዳዲስ አማኞችን ወደ ቤተ ክርስቲያን ለመጥራት የሚያስችል ስልት ለመንደፍ ያግዛል። I. ስብከተ ወንጌል፥ የኦይኮስ (የቤት) ጒዳይ • የኦይኮስ ሁኔታ፥ በስብከተ ወንጌል ምስክርነት ውስጥ ትልቅ ስፍራ የሚሰጠው ማኅበራዊ ገጽታ ነው።

1 Adapted from a seminar by Rev. Dr. Don L. Davis in Ripe for Harvest , pp. 242-247.

Made with FlippingBook - Share PDF online